Song Lyrics

እንፀልይ

Feben Demissie
Selfu Yegziabher New
ጊዜው እየከፋ ሲሄድ ሰው ምን ያደርጋል ጥፋት ሲበዛ ወዴት ይሸሻል መተማመን ጠፍቶ ጥላቻ ሲበረታ የተለፋበት ሁሉ ድርምስምስ ሲል ቀና ነው የተባለው ቅጡ ሲጠፋ ሰው ግራ ተጋብቶ ጭንግር???ጭምር??? ሲለው ወደማን ነው የሚያየው አዝ፦ እንጸልይ ጸሎት የሚሰማ አምላክ አለ እንጸልይ ሳንታክት እንጸልይ ፍርድን የሚወድድ አምላክ አለ በሰማይ (2x) በድህነት ቀመር ተጠፍሮ ህዝብ በድካም ጅራፍ ሲገረፍ ሞትን እንደጨለማ ምድራችንን ሲከብ አንዱ ከአንዱ ሲጋደል አለቆች አልፈቱም ይህን እንቆቅልሽ ከአዋቂቆችም ምክር አልተገኘም ነገሥታት እነርሱ ተሰወረባቸው ድንግዝግዝ አለ ቀኑ አዝ፦ እንጸልይ ጸሎት የሚሰማ አምላክ አለ እንጸልይ ሳንታክት እንጸልይ ፍርድን የሚወድድ አምላክ አለ በሰማይ (2x) እንጸልይ በስሜ የተጠሩ ህዝቤ ራሳቸውን አዋርደው ቢጸልዩ ከሰማይ ሆኜ እሰማለሁ ምድራቸውን እፈውሳለሁ ብሏል ጌታ (2x) አዝ፦ እንጸልይ ጸሎት የሚሰማ አምላክ አለ እንጸልይ ሳንታክት እንጸልይ ፍርድን የሚወድድ አምላክ አለ በሰማይ (2x) እንጸልይ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection