Song Lyrics

ያቺ ጉጠት

Eyerusalem Negiya
Yetsegawun Kuribet
ሳበኝ ወዳንተ እሮጣለሁ መልካሙ እረኛ ድምፅህን እየሰማሁ እከተልሀለሁ ሳበኝ ወዳንተ እሮጣለሁ መልካሙ እረኛ ኮቴህን እየሰማሁ እከተልሀለሁ ያቺ ጉጠት ኢሳያስን የዳሰሰች አንደበቱን ንግግሩን የለወጠች ዛሬም ትምጣ በነፍሰ ስጋ በመንፈሴ እንዲወገድ ከህይወቴ ድንዛዜ ሀይል ያስፈልገኛል የእግዚአብሔር እሳት ሙሴ በቁጥቋጦ ውስጥ ስትነድድ ያያት ክብርህ ናፍቆኛል እንዲገለጥ በህይወቴ አንድ ጊዜ ንካኝ ይለወጥ ህይወቴ ከአለም መጎምዠት ከስጋዊ መሻት ውስጡ ወና ባዶ ውሸትና ቅዠት ከምናቡ አለም በአምሮት ከመስከር ህልሜ መና ሆኖ በምኞት እንዳይቀር ነጥቆ በሚያወጣው ከዘቀጠው ሀሳብ በመንፈስህ ላምልጥ ከሌለበት እረብ ክብርህ ናፍቆኛል እንዲገለጥ በህይወቴ አንድ ጊዜ ንካኝ ይለወጥ ህይወቴ የመንፈስህ እሳት የክብርህ ሙላት ሲያገኘኝ ሲነካኝ ያንተ መገኘት እንደ ሌላ ሰው እለወጣለሁ ደጋግመህ ንካኝ መቼ እረካለሁ እንደ ሌላ ሰው እለወጣለሁ ደጋግመህ ንካኝ መቼ እረካለሁ ህልውናህ መንፈስህ ነፍሴን ደስ ያሰኛል ህልውናህ መገኘትህ ነፍሴን ያረካታል የናፈቀኝ የተጠማሁት የምፈልገው የሚናፍቀኝ ክብርህን ነው ክብርህን መንፈስህን ነው ክብርህ ክብርህን ነው ክብርህን መንፈስህን ነው መንፈስህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection