እግዚአብሔር እንደሰው ቢሆን ኖሮ እንደ ሰው ቢያስብ ኖሮ ኃጢአቴን ልናዘዝ ህሊናዬ ሲወቅሰኝ ምህረትም ልማጠነው ደጅባስጠናኝ ውድቀቴ ሳይገደው ባላገጠ ፊቱ በጠቆረ ፍቅሩ ቀዝቅዞብኝ ድምጹ በሻከረ እንኳንስ ልጁ ሊያረገኝ ሥሙን ለመጥራት ባስከፈለኝ (2x) እንኳንስ ቤቱ ለመኖር ከደጁ መጣል በተሳነኝ ከደጁ መጣል በናፈቀኝ አዝ፦ ግን እግዚአብሔር እንደሰው አይደለም ከቶ እግዚአብሔር እንደሰው አይደለም ምህረት ቸርነቱ ወሰን ቁጥር የለው ከወዳጅም ወዳጅ ፍቅሩ ብዙ ነው እግዚአብሔር እንደ ሰው እንደ ሥጋ ለባሽ የወደቀን አይቶ እንዳላየ አይሸሽ እንደ ሰው አይደለም (4x) እንደ ሰው አይደለም ፍቅሩ አያረጅም እንደ ሰው አይደለም አይለዋወጥም እንደ ሰው አይደለም ፍቅሩ አያረጅም እንደ ሰው አይደለም አይለዋወጥም እግዚአብሔር እንደ ሰው ቢያይ ኖሮ እንደ ሰው ቢያስብ ኖሮ ያለኝን ሁሉ ሳጣ ሲጐድል ሙሉ ቤቴ ከንፈር ቢመጥልኝ ርቆ ከአጠገቤ ባሕሪው ተለውጦ ቀስ እአለ በሽሽ በራቀ ወዳጅነት ቀርቶ አዛኝ በመሰለ ነፍሴን ሲከፋት ዝም ስል ሃዘኔ ንቀት ቢመስል (2x) ውስጤ ማቅ ለብሶ ከሰው ቢያርቅ እንደኮራሁ ቢያስበኝ እንደተኩራራሁ ቢያስበኝ አዝ፦ ግን እግዚአብሔር እንደሰው አይደለም ከቶ እግዚአብሔር እንደሰው አይደለም ይረዳል ይረዳል የውስጥን ስብራት ሀዘን ይጠግናል እግዚአብሔር እንደ ሰው እንደ ሥጋ ለባሽ የወደቀን አይቶ እንዳላየ አይሸሽ እንደ ሰው አይደለም (4x) እንደ ሰው አይደለም ፍቅሩ አያረጅም እንደ ሰው አይደለም አይለዋወጥም እንደ ሰው አይደለም ፍቅሩ አያረጅም እንደ ሰው አይደለም አይለዋወጥም