ቀድሞ ወፉ ሳይጮህ ጠዋት በማለዳ ጌታ ፈጥኖ መጣ ልጆቹን ሊያነቃ ማን ይላከኝ ብሎ ስራውን ሊሰራ በጠዋት ለወደደው ተሰጠው አደራ ዓለም ቀውጢ ሆና እጅግ ተጨንቃለች በል ስጣት መድሃኒት ፈውስ አታተማለች ፍጠን ልጄ አለው ሳይመሽብህ ቀኑ መርቆ ሰደደው እንዲቀና መንገዱ ቢነቃም ማለዳ እጅ እግሬን እያለ ከቤቱ የወጣው አርፍዶ ነበረ ከመንገዱ ሳለ ገና ሳያጋምስ ጠለቀበት ጀምበር ከቦታው ሳይደርስ መራመድ ቢጀምር ብርሃኑ ጨላልሞ ተሰብሮ ወደቀ መልዕክቱን አንግቦ ምን ይጠቅመው ታዲያ በጸጸት መንደዱ መሮጡ በበጀው ብሩህ ሳለ ቀኑ አዝ፦ ቀን ሳለ ልሩጥ ሳይጨልም ብርሃኑ ሳይመጣ ጽልመቱ ሳይዘኝ ድባቡ (ልሩጥ) ወገግ ሲል ቀኑ (ልሩጥ) ሳይጠልቅ ጀምበሩ (ልሩጥ) ሳይደክም ጉልበቴ (ልሩጥ) ሳይዝል ሰውነቴ ሳይደክም (ልሩጥ) ጉልበቴ ሳይዝል ሰውነቴ ሳይመጣ (ልሩጥ) ጽልመቱ ሳይዘኝ ድባቡ ትንፋሽ ያለው ፍጥረት መሽቶለት ሲነጋ አለው ብዙ ተግባር ዛሬን እንዲተጋ አለው ብዙ ልፋት አለው ብዙ ጥረት ነገም ሌላ ቀን ነው ሌላ ደግሞ ሂደት ሳይተጉበት ዛሬ ሳይኖሩ ለዛሬ አንዳች ሳይጨበጥ ሲገፋ ያ ዕድሜ ምን ሊፈይድ ታዲያ በጸጸት መንደዱ መሮጡ ይበጃል ምቹ ሳለ ቀኑ አዝ፦ ቀን ሳለ ልሩጥ ሳይጨልም ብርሃኑ ሳይመጣ ጽልመቱ ሳይዘኝ ድባቡ (ልሩጥ) ወገግ ሲል ቀኑ (ልሩጥ) ሳይጠልቅ ጀምበሩ (ልሩጥ) ሳይደክም ጉልበቴ (ልሩጥ) ሳይዝል ሰውነቴ ሳይደክም (ልሩጥ) ጉልበቴ ሳይዝል ሰውነቴ ሳይመጣ (ልሩጥ) ጽልመቱ ሳይዘኝ ድባቡ እራሱን የሚወቅስ እራሱንም ሚዘልፍ ስንቱ ነው በቤቱ እለት በእለት ሲያልፍ ዛሬ የትላንት ውጤት መሆኑ ሚገባው አንዳንዱ ዘግይቶ በረፋዱ ላይ ነው እንግዲያው በቀረው በተረፈው ዘመን ኋለእኛው ይበርታ ይበቀል ትናንትን የወደቀ ይነሳ ይሆን አዲስ ሃይልን በሚሰጠው በእግዚአብሔር መንፈስ