Song Lyrics

የዜማ ጊዜ

ዘሩን ከእምባው ጋር የዘራ እርኮ ተወስዶ የፈራ ማሲንቆን አፍሮ የደበቀ ጠላቱ ወድቆ ደቀቀ ቡቃያ ደርሶ አፈራ ወይኑ ዘለላው ጐመራ በደስታ ነዶውን አጨደ ማሲንቆውን አወረደ አዝ፦ የጉብኝቴ ዘመን ፈጠነ የዜማ ጊዜ እየደረሰ እንባዬ ታበሰ ምርኮዬን መለሰ የልቤ ደረሰ ድል አስታጠቀኝ አሄ ጠላት አፈረ (2x) ዳርቻዬን አሰፋልኝ ካዝማዬንም አጸናልኝ ይሄው ቆመዋል አግሮቼ ምርኩዝ ሆኖልኝ አባቴ ተሰብሯል የሃፍረት ቀንበሬ ሞልቶታል አፌን ዝማሬ ሞገስ በረከት ከደጅ ገብቷል ኢየሱስ ወዳጄ አዝ፦ የጉብኝቴ ዘመን ፈጠነ የዜማ ጊዜ እየደረሰ እንባዬ ታበሰ ምርኮዬን መለሰ የልቤ ደረሰ ድል አስታጠቀኝ እሰይ/አሜን ጠላት አፈረ (2x) ነፍሴ ሆይ ደስ ይበልሽ ለምሥጋና ደግሞ ተነሽ አጥንቶቼ እግዚአብሔርን ባርኩ ታላቅ ስሙን በሉ አወድሱ አካላቶቼ በድል ዘምሩ በነጋ ጠባ ስራውን አብስሩ ያላሳፈረኝ ሞገስ የሆነኝ ጌታ ነውና ዛሬም ያገዘኝ በምሥጋን (3x) ልቤ ተነሳ በምሥጋን (3x) መጣሁ እንደገና በምሥጋና (3x) ድል አለ እንደገና ልቤ በሃሴት በደስታ ፈሰሰ ቀኔ ዕልልታ ከአለት እቃቃት ወጥቼ ድምጼን ላሰማ ለአምላኬ ጭጋጉ ይሄው ገፈፈ ሀዘን ትካዜው አለፈ ላሞግሰው እንደገና . (1) . ዝማሬ ምሥጋና አዝ፦ የጉብኝቴ ዘመን ፈጠነ የዜማ ጊዜ እየደረሰ እንባዬ ታበሰ ምርኮዬን መለሰ የልቤ ደረሰ ድል አስታጠቀኝ እሰይ/አሜን ጠላት አፈረ (2x) ነፍሴ ሆይ ደስ ይበልሽ ለምሥጋና ደግሞ ተነሽ አጥንቶቼ እግዚአብሔርን ባርኩ ታላቅ ስሙን በሉ አወድሱ አካላቶቼ በድል ዘምሩ በነጋ ጠባ ስራውን አብስሩ ያላሳፈረኝ ሞገስ የሆነኝ ጌታ ነውና ዛሬም ያገዘኝ በምሥጋን (3x) ልቤ ተነሳ በምሥጋን (3x) መጣሁ እንደገና በምሥጋና (3x) ድል አለ እንደገና በምሥጋን (3x) ልቤ ተነሳ በምሥጋን (3x) መጣሁ እንደገና በምሥጋና (3x) ድል አለ እንደገና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection