Song Lyrics

ሠማዩ ነገረኝ

አዝ፦ የእግዚአብሔርን መኖር ሠማዩ ነገረኝ ምድሩ አወራኝ ቀኑ ምሽት ሲሆን ሌሊቱ ሲነጋ አረጋገጠልኝ ያለ የነበረ ደግሞም የሚኖረው ዘለዓለም በክብሩ ፍጥረታት በሙሉ ስለህልውናው ይመሰክራሉ (2x) ለሚመረመር ለባዕድ አእምሮ የእግዚአብሔር ነገር በከንቱ መድከም መሆን ተላላ እጅግ መሞኘት ሳይዩ የሚያምኑ ብጹአን ሆኑ ለስሙ አምነው በቤቱ ጸኑ መዳን አገኙ ከሞት ተረፉ ከዚህ ዓለም ይልቅ ብዙ አተረፉ ለእኛ ለደካሞች ይሄ እውነት በራ ለእኛ ለምስኪኖች ለእኛ ለደካሞች ይሄ እውነት ታየ ለእኛ ለምስኪኖች አዝ፦ የእግዚአብሔርን መኖር ሠማዩ ነገረኝ ምድሩ አወራኝ ቀኑ ምሽት ሲሆን ሌሊቱ ሲነጋ አረጋገጠልኝ ያለ የነበረ ደግሞም የሚኖረው ዘለዓለም በክብሩ ፍጥረታት በሙሉ ስለህልውናው ይመሰክራሉ (2x) ያወቀ ሊመስል ጠቢብ የሆነ እጅግ የላቀ ሰነፍ መሆኑን ከሰው ሊደብቅ ልቡ እያወቀ ምኞቱን ለማድረክ አምላኩን ክዶ ከህሊና ሙግት ሊያመልጥ ፈልጐ ድፍረት ቢሞላው በውስጡ ክፉ ከንቱ ሃሳቡን አወራ አፉ ሞኞችና ድሆች እግዚአብሔር (2x) ኧረ እንደው ይላሉ ብሎ ደመደመ ተስፋ ቢሶች ናቸው ጥበብን ስላጡ (2x) ነፍሱ ጌታን ብትፈልገው እራሱን አምላክ አደረገው የእግዜር ፍጥረታት አካላቱ በድፍረት ነው ክህደቱ የወንዙ የተራራው የባሕር የውቅያኖስ ፈጣሪውን ያሳያል የፍጥረት ግርማ ሞገስ አለ ይላል እግዚአብሔር አሃ አለ ይላሉ እግዚአብሔር አለ ጌታ እግዚአብሔር ኦሆ አለ ጌታ እግዚአብሔር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection