ምሥጋና ልሰዋ በተዋበ ዜማ ሁሉ በሚቀለው ሊዘምር ከእኔ ጋር ደስ ብሎኝ ተነሳሁ ልመታ ከበሮ አምላኬ አርቆታል የልቤን እሮሮ አዝ፦ (ኦሆኦሆሆ) ደስ ያለው ይዘምር (ኦሆኦሆሆ) ተሰብሮለት ቀንበር (ኦሆኦሆሆ) ይሰዋ ምሥጋና (ኦሆኦሆሆ) ለጌታ እንደገና ላከበረኝ ጌታ በምወደው ዜማ በሚገባኝ ቋንቋ ቅኔን በሙገሳ ምቱልኝ ከበሮ የታለ ዕልልታ በማዕረግ መዝሙር ላክብረው በሆታ የባርያዪቱን ውርደት አምላኳ አየና ስድብ ነቀፋዋን አስቦ እንደገና እግዚአብሔር ከሰማይ ቀንን ሲቆጥርላት መገፋቷን አይቶ ዛሬ ደረሰላት ቀንዴ ከፍ ብሏል አፌም ይዘምራል ጓዳዬ በቅኔ በዝማሬ ደምቋል አዝ፦ (ኦሆኦሆሆ) ደስ ያለው ይዘምር (ኦሆኦሆሆ) ተሰብሮለት ቀንበር (ኦሆኦሆሆ) ይሰዋ ምሥጋና (ኦሆኦሆሆ) ለጌታ እንደገና ላከበረኝ ጌታ በምወደው ዜማ በሚገባኝ ቋንቋ ቅኔን በሙገሳ ምቱልኝ ከበሮ የታለ ዕልልታ በማዕረግ መዝሙር ላክብረው በሆታ የእንባ ስቅታዬ መርዶ በወጣበት ዛሬ ግን ከቤቴ ምሥጋናን ሞላበት አምላኬ በክብሩ ወደ እልፍኜ ገብቷል የዕልልታዬ ድምጽ ከሩቁ ይጠራል ወዳጅ ዘመዶቼ ጌታ ይሰራልኝን አይተው ከእኔ ጋራ አከበሩት ውዴን አዝ፦ (ኦሆኦሆሆ) ደስ ያለው ይዘምር (ኦሆኦሆሆ) ሆኖ ከእኒ እጋራ (ኦሆኦሆሆ) የተደረገለት (ኦሆኦሆሆ) እስቲ ማን አለና ላከበረኝ ጌታ በምወደው ዜማ በሚገባኝ ቋንቋ ቅኔን በሙገሳ ምቱልኝ ከበሮ የታለ ዕልልታ በማዕረግ መዝሙር ላክብረው በሆታ ልስገድ በሽብሸባ ይጨመር ጭብጨባ ይህ አይበቃምና መቅደስ ውስጥ ስገባ ምቱልኝ ከበሮ የታለ ዕልልታ በማዕረግ መዝሙር ላክብረው በሆታ (2x)