አዝ፦ ነፍሴ አጥታልህ ለአንተ መግለጫ እንዲህ ትላለች ቢያረካህ ብላ (2x) ሕይወቴ ያክብርህ በቀረው ዘመኔ ከእንግዲህ አይኑረኝ ምኖረው ለእኔ (2x) ፍቅርህ ልቤን ከነካው ከለወጠው ሰንብቷል ያኔ ለጋ ሳለሁ ከውስጠቴ ዘልቆ ገብቶ ቤቱ አስቀረኝ ነፍሴን ማርኮ (2x) አዝ፦ ነፍሴ አጥታልህ ለአንተ መግለጫ እንዲህ ትላለች ቢያረካህ ብላ (2x) ሕይወቴ ያክብርህ በቀረው ዘመኔ ከእንግዲህ አይኑረኝ ምኖረው ለእኔ (2x) ፀጋህና ምህረትህ ለመዳኔ ምክንያት ሆነኝ ለማምለጥ ከኩነኔ በመስቀል ላይ በሰራኀው ታላቅ ስራ እኖራለሁ በመስቀል ላይ በሰራኀው ታላቅ /ገድል ይሄው አለሁ አዝ፦ ነፍሴ አጥታልህ ለአንተ መግለጫ እንዲህ ትላለች ቢያረካህ ብላ (2x) ሕይወቴ ያክብርህ በቀረው ዘመኔ ከእንግዲህ አይኑረኝ ምኖረው ለእኔ (2x) ወደእግዚአብሔር የሚያደርሰው እውነት ሕይወት መንገድ ኢየሱስ ነው የሰው ልጅ በከንቱ እንዳይለፋ ሁሉን ፈጸመ ሰጠው ተስፋ የዳነ ሰው ጌታ ያለው በማንነቱ ከቶ አይደለም መወደዱ መመረጡ ዓለም ገና ሳይፈጠር በክርስቶስ የመረጠውን አጸደቀው አከበረው ማንም እንዳይመካ በስራው አይደለም ማንም እንዳይታበይ በስራው አይደለም (2x)