Song Lyrics

ወለል ያለ

Eyerusalem Negiya
Yetsegawun Kuribet
ወገግታዬ ነው የማለዳ ጮራዬ ከርሱ የተነሳ በራ ጨለማዬ ወገግታዬ ነው የማለዳ ጮራዬ ከርሱ የተነሳ በራ ጨለማዬ ጠአመ ቢስ ልሳኔ አንደበቴም ገራ ህይወቴ ጨፍጋጋ እንዳይሆን መራራ አመዴን አራግፎ ወዛም ያደረገኝ በሰዎች ሁሉ ፊት በሞገስ አቆመኝ ደብዛዛው መልኬ ደመቀ በስሙ ጭንጋፉ ገፄ ተዋበ በደሙ በድቅድቁ ለሊት በማይሸፈን ፊት እንዳብለጨልጭ ጌታዬን ልክ እንደ መስታወት የፊቱ ብርሀን ፍንትው ያለ ጮራ እየጨመረ መጣ በላዬ ላይ በራ የፊቱ ብርሀን ወለል ያለ ጮራ እየጨመረ መጣ በላዬ ላይ በራ በራ(#2) የህይወቴ ጭጋግ ወገግ አለ በራ ፈካ በራ(#2) የህይወቴ ጭጋግ ወገግ አለ በራ በቀን ከሚበረው አስደንጋጭ ፍላፃ ነፍሴ እርፍ አለች በአንተ ወጥታ ነፃ የቀትሩ ጋኔን እንዳያስፈራራኝ መቅሰፍት ወደ ቤቴ እንዳይገባ ጋረደኝ መላዕክቱን ስለኔ እያዘዛቸው እንዳልሰናከል ያዙኝ በእጆቻቸው ተኩላ እና እባቡን እረጋግጬ ድል አድራጊ ሆንኩ በኢየሱስ ወጥመዱን አምልጬ በባላንጣዬ ፊት ራሴን ቀብቶታል ያስፈራኝ ጠላቴ በተራው ፈርቶኛል በባላንጣዬ ፊት ራሴን ቀብቶታል ያስፈራኝ ጠላቴ በተራው ፈርቶኛል ፀና (*2) የህይወቴ ካስማ አለቱ ላይ ፀና ኦሆሆ ፀና (*2) የህይወቴ ካስማ አለቱ ላይ ፀና ማረፊያዬ ነው የቀትር ጥላዬ ከርሱ የተነሳ ፈርቶኛል ጠላቴ ማረፊያዬ ነው የቀትር ጥላዬ ከርሱ የተነሳ ፈርቶኛል ጠላቴ ምን ይዋጠኝ ብዬ ለነገ እንዳልሰጋ ፅኑ የተስፋ ቃል እኔ አለኝ እሱጋ በእጄ የያዝኩት ቢወድቅ ቢናድ የካብኩትም ኢየሱስ ስላለኝ አልርበተበትም በትርህ ምርኩዜ ለሽምግልናዬ ቀሪ ሀብቴ ነው ቢጎብጥ ጀርባዬ እስከ ሽበቴ ይሸከመኛል የማታ የማታ መጦሪያዬ ኢየሱስ ሆኖኛል ቸርነት ምህረቱ ሁሌ ይከተሉኛል ዘልአለም በቤቱ አዝልቆ ያኖረኛል ቸርነት ምህረቱ ሁሌ ይከተሉኛል ዘልአለም በቤቱ አዝልቆ ያኖረኛል ፀና (*2) የህይወቴ ካስማ አለቱ ላይ ፀና ኦሆሆ ፀና (*2) የህይወቴ ካስማ አለቱ ላይ ፀና ቱሩፋቴ ነው የማታ እንጀራዬ ከርሱ የተነሳ ያምራል እርጅናዬ ቱሩፋቴ ነው የማታ እንጀራዬ ከርሱ የተነሳ ያምራል እርጅናዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection