Song Lyrics

የእሩቅ አላሚ

Eyerusalem Negiya
Yetsegawun Kuribet
የሩቅ አላሚ ነኝ ግን የቅርብ አዳሪ የሩቅ አሳቢ ነኝ ግን የቅርብ ተጓዥ ነዋሪ ሰፋሪ የፈቃድን ሚስጥር እሻና በብርቱ ግን ልቤ ሊኖረው አወይ ማመንታቱ በውስጥ ማንነቴ በራለሁ ከሰማይ ስጋዬ ጎትቶ ያወርደኛል ከላይ ፍቅርህ ትዝ ሲለኝ ውስጤ ይነካና አይኔ እንባ ያፈሳል ትናፍቀኝና ነፍሴ ተነቃቅታ አንተኑን ስታስብ መንፈሴ ወዲያውኑ ይጋልባል ሽቅብ መንፈሳዊነቴ ያኔ ሲበረታ ሀሌሉያ እያልኩ ከምድር ስፋታ ያልማል ይመኛል ሰማዩን ምናቤ ከደመናው በላይ ይሄዳል ሀሳቤ ያን ግዜ እንዳልደክም ምዬ ተገዝቼ ፈለግህን ልከተል ለራስ ቃል ገብቼ በአለም ማዕበል ሲመታ ግለቴ መች ይታወቀኛል ሲደክም ህይወቴ። በኑሮ ገጠመኝ ከፍና ዝቅ ስል በወጣሁበት ልክ እየኝ ሳሽቆለቁል በረታሁኝ እያልኩ ዝዬ እገኛለሁ በሁለቱ ክበብ ላይ እሽከረከራለሁ ከዚህ ሟች ስጋዬ የሚለየኝ ማነው? ጥማቴም ረሀቤም አንተን ለመምሰል ነው እንደማትጥለኝ በእርግጥ አውቃለሁ ግን አንዳንዴ ራሴ ማመን እፈራለሁ። ድሮም ፀጋህ እንጂ እኔ የቻልኩት ምንድነው? ሀይልን በምትሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ ድሮም ፀጋህ እንጂ እኔ የቻልኩት ምንድነው ሀይልን በምትሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ ቢዝል ቢደክም ስጋዬ ዳግም ሊበረታ በድካሜ ምትራራ ደጉ የኔ ጌታ እጄን በእጅህ እንደያዝክ እስከ መጨረሻው እያገዝከኝ በፀጋህ ዘልቄ እሄዳለሁ ፀጋህ እየረዳኝ እያገዝከኝ ባንተ ሁሉን እችላለሁ እችላለሁኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection