Song Lyrics

ወዶኛልና

Eyerusalem Negiya
Yetsegawun Kuribet
ምን ውጦኝ ነበር አንተን ባላገኝ ባትቀበለኝ ልጅ ባታረገኝ አሄሄ ሰጥተኸኝ ጥበብ ክህሎት ችሎታ አምላኬን ትቼ ለሰው ሆይ ሆይታ አሄሄ ነበር እጣዬ አይኔ ባይበራ የሲዖል ማገዶ ኑሮ ከሞት ጋር በራልኝና የህይወት መንገድ ኑሮ ጀመርኩኝ ባንተ ስወደድ ዛሬ ግን ለኢየሱስ እዘምራለሁ እዘምራለሁ ዘምሬ የማልጠግበው ስለርሱ ነው ዛሬ ግን ለክብሩ አወራለሁ አወራለሁ አውርቼ የማልጠግበው ስለርሱ ነው ወዶኛልና አዳናት ነፍሴን አረ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን ወዶኛልና ድናለች ነፍሴ እስቲ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን ከህይወት ምንጭ ውሀ ፈልቆ ጠጣሁና ጥሜ ቆረጠልኝ ዳግም ላልጠማ የክብሩ ነፀብራቅ በላዬ ላይ በርቶ ከክብር ወደ ክብር አሻገረኝ መርቶ ወዶኛልና አዳናት ነፍሴን አረ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን ወዶኛልና ድናለች ነፍሴ እስቲ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን የፊቱ ብርሀን አበራ በህይወቴ ጉሙ በነነ ፈካ ህይወቴ ተጥለቀለኩኝ በደስታ በሀሴት ከላይ ወረደልኝ ፍፁም በረከት ወዶኛልና አዳናት ነፍሴን አረ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን ወዶኛልና ድናለች ነፍሴ እስቲ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን ማን ልበለው ውዴን ምን ልበለው አንጀቴን የሚያርስ ማብራሪያ ባገኘሁ ማን ልበለው ውዴን ደስ እንዲለው አንጀቴን የሚያርስ ዜማ ቃል ባገኘሁ ከዘልአለም ማዕድ ከእንጀራው በልቼ ላልራብ ረካሁ ኢየሱስን አግኝቼ የመቅበዝበዝ ህይወት ከእንግዲህ አበቃ አይኖቼን ከፈተ ሙት መንፈሴ ነቃ ወዶኛልና አዳናት ነፍሴን አረ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን ወዶኛልና ድናለች ነፍሴ እስቲ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን ማን ልበለው ውዴን ምን ልበለው አንጀቴን የሚያርስ ማብራሪያ ባገኘሁ ማን ልበለው ውዴን ደስ እንዲለው አንጀቴን የሚያርስ ዜማ ቃል ባገኘሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection