Song Lyrics

ይችላል

Eyerusalem Negiya
Yetsegawun Kuribet
እናንተ ደካሞች ብዙ ሸክም የከበዳችሁ ወደኔ ቅረቡ ከቀንበራችሁ ላሳርፋችሁ ብሏልና ጌታ ሸክሜን ሁሉ አንድም ሳላስቀር አራግፋለሁ ጭንቀቴን ሁሉ ከእግሩ ስር እኔን ያጎበጠኝ በርሱ ፊት ምንድነው አልፈታም ሚለው ችግሬ የትኛው ነው ጥያቄዬን ሁሉ እሰድዳለሁ ወደላይ ለእርሱ አስረክቤ እኔ እላለሁ እፎይ ይችላል ( #4 ) ይችላል ሽባውን መተርተር ይችላል ዲዳውን ማናገር ይችላል ተራራውን መናድ ይችላል ደመናውን ማውረድ አለቀልኝ ብዬ ያከተመው ነገሬን ይዤ ስለምን ልቀመጥ አንተ እያለህ በሀዘን ተክዤ ትናንትን ስትሰራ ስታደርግ በአይኔ አይቼ ስለምን ልጠርጥር ዛሬ የተራራውን ትልቀት ፈርቼ ተራራው ለኔ እንጂ ባንተ ፊት ምንድነው የሚገዳደርህ ሀይል የትኛው ነው አንዳች ነገር የለም ካንተ አቅም በላይ ሁሉን የምትችል ጌታ አይደለህም ወይ ይችላል ( #4 ) ይችላል እንቆቅልሽ መፍታት ይችላል ያዘነን ማፅናናት ይችላል የወደቀን ማንሳት ይችላል ጨለማውን ማብራት ከበበኝ በላይ ያንተ ትልቅነት ይታየኛል ያንተ ትልቅነት ይከብድብኛል አምንሀለሁ ጌታ ሁሉ ይቻልሀል ምን ተስኖህ ሁሉ ይቻልሀል ምን ያቅትሀል? ከበደኝ በላይ ያንተ ትልቅነት ይታየኛል ያንተ ትልቅነት ይገዝፍብኛል አምንሀለሁ አባ ሁሉ ይቻልሀል ምን ተስኖህ ሁሉ ይቻልሀል ምን ያቅትሀል? ትሰራለህ ታደርጋለህ የሚሳንህ የለም ትተክላለህ ትነቅላለህ ከልካይ የለብህም ክንደ ብርቱ አምላክ ነህ ሁሉን ትችላለህ ክንደ ብርቱ አምላክ ነህ ሁሉን ትችላለህ ትሰራለህ ታደርጋለህ የሚሳንህ የለም ትተክላለህ ትነቅላለህ ከልካይ የለብህም ክንደ ብርቱ አምላክ ነህ ሁሉን ትችላለህ ኤልሻዳይ አምላክ ነህ ሁሉን ትችላለህ ትችላለህ የጠፋን መመለስ ትችላለህ በሽታን መፈወስ ትችላለህ ሸለቆን መሙላት ትችላለህ የሞተን ማስነሳት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection