Song Lyrics

ሞት ሆይ

Eyerusalem Negiya
Yetsegawun Kuribet
ወጥመዱን ዘርግቶ ነፍሳትን ሲጠልፍ የሰውን ልጅ በሙሉ በሀጥያት ሲነድፍ ሲፎክር ሲዘብት ማን አለብኝ ብሎ ዲያብሎስ ወደቀ ዛሬ ድል ተነስቶ ወደ ሲዖል ወርዶ መንጋጋው ፈልቅቆ ነፍሳትን አዳነ ኢየሱስ ተናጥቆ የሞት ፍርሀት ቀንበር ቆሌው ተገፈፈ በቃ አለቀለት ሰይጣን ተሸነፈ ሞት ሆይ የታለ ማሰሪያህ ሲዖል ሆይ የታለ መውጊያህ ሞት ሆይ የታል ጩኸትህ ሲዖል ሆይ የታለ ቀስትህ ይሄ ሁሉ ክብር ይሄ ሁሉ ዝና(*2) ኦኦ ዝና ተገብቶሀልና ጌታ አንተ ነህ ገናና ገና ኦኦ ገና ሞትን ድል የነሳ የይሁድ አንበሳ ሞትን ያሸነፈው ክብር የተረፈው እንግዲህ የአዳም ዘር ትንሳኤ ሆነለት በኢየሱስ መሞት ሞት ተሸነፈለት ምድር እልል ትበል ጌታዋ ተነስቷል በትንሳኤው ጉልበት መዳን መጥቶላታል በመከራው ብዛት በጭንቅ በፍዳው ለኔ ለአንቺ ለአንተ ነው እንዲህ የተጎዳው በእርሱ ያመነ ማንም እንዳይጠፋ አንድያ ልጁ ነው የእግዚአብሔር ስጦታ ሞት ሆይ የታል ማሰሪያህ ሲዖል ሆይ የታለ መውጊያህ ሞት ሆይ የታል ጩኸትህ ሲዖል ሆይ የታለ ቀስትህ ጩኸት ማስፈራራት ዋይታና ሁካታ ኦኦ ሁካታ ሞትን ድል በነሳ በጌቶቹ ጌታ ጌታ ኦኦ ጌታ ፀጥ አለ ድንፋታው ሽለላው ፉከራው ስልጣኑን ገፈፈው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection