Song Lyrics

እረግረጉ ደረቀ

Eyerusalem Negiya
Yetsegawun Kuribet
እግዚአብሔር ከኔ ጋር ባይሆንማ ኖሮ የጠላቴ ቁጣ በኔ ላይ በርትቶ በህይወት ሳለሁኝ በዋጠኝ ነበረ ታሪኬን ሊያስቀረው እያለ እንዳልነበረ ለጥርሱ ንክሻ አልተተውኩም እንዳሰበው ክፉ አላገኘኝም ለጥርሱ ንክሻ አልተተውኩም እንዳሰበው ጠላት አላጠፋኝም ጠላቴማ ሊለያየኝ ስንት ጊዜ ሞከረ ሊነጥለኝ ስንት ጊዜ ጣረ ጌታ ጣልቃ እየገባ ምክሩን እያፈረሰ የሸፈተው ልቤን ወደራሱ መለሰ በፀሎቴ አለፍኩት አልልም ያንን ሁሉ ወጀብ በጉልበቴስ መች በተንኩት አስፈሪውን አጀብ በፅናቴ ተወጣሁት አልልም ያን ዳገት አቀበት በብልጠቴስ መች ሾለኩኝ ከዛ ሁሉ ውድቀት ፀጋህ ተትረፍርፎ ምህረትህ በዝቶልኝ የማልችለው ተቻለኝ ከባዱ ቀለለኝ እረግረጉ ደረቀ ጎርባጣውም ቀና የዘመመው ማገሬ እንደገና ፀና ሰባራውን ድልድይ እየገጠመ ጎርፉን እየገደበ ስፍገመገም እጄን በእጁ ይዞ እግሬን አሻገረ በስሙ አለት ላይ አፀናኝና እንዳወራ የሱን ዝና ዜማን እና ቅኔን አስታጠቀኝ ዘምርለታለሁ ገና አዜምለታለሁ ገና እቀኝለታለሁ ገና እኖርለታለሁ ገና አገለግላለሁ ገና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection