Song Lyrics

አወራታለሁ

Eyerusalem Negiya
Yetsegawun Kuribet
ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው የሚወደድ ማይጠገብ ለሚጠራው ነፍሴን ከሞት መለሰ ፍቅርህ እንደ ጅረት እየፈሰሰ መንፈሴን አረሰረሰ ህይወቴን እየፈወሰ መንፈሴን አረሰረሰ ስጋዬን እየፈወሰ ለስብራቴ ፍቱን መድሀኒቴ መድመቂያ ካባዬ ለማንነቴ ስምህ ነው ትምክህቴ መቆሚያ አለቴ ማገሩ ለቤቴ ፅኑ መሰረቴ የክብር ንጉስ ነህ ደጉ ኢየሱስ ለዘልአለም ንገስ በመንበሬ በኑሮዬ በሰገነቴ በከፍታዬ ለዘላለም ንገስ አንተ የክብር ንጉስ ወደዱህ ወደዱህ ያዩህ የቀመሱህ ባንተ ደስ አላቸው ሀሴት አደረጉ መአዛህ መልካም ነው ስንቱን ለወጠ ስንቱን አጣፈጠ ፍቅርህ ልዩ ነው ስንቱን ለወጠ ስንቱን አጣፈጠ የእኔነቴ ማዕረግ የክብር መጠሪያዬ ኢየሱስ አንተው ነህ ጌጤ መዋቢያዬ ነፍሴ እንድታውቅህ አንተን እሰብካታለሁ ልቤም እንዲወድህ ሁሌ አስብሀለሁ አወራታለሁ ለነፍሴ ስላንተ አብዝቼ ሁልጊዜ እነግረዋለሁ ለልቤ ፍቅርህ እንዲበረታ በሀሳቤ አወራታለሁ ለነፍሴ ስላንተ አብዝቼ ሁልጊዜ እነግረዋለሁ ለልቤ ፍቅርህ እንዲበረታ በሀሳቤ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection