Song Lyrics

የጸጋውን ቁርበት

Yetsegawun Kuribet

Eyerusalem Negiya
Yetsegawun Kuribet
የፍጥረት በኩር መጀመሪያ ፍፃሜ የሆነ መደምደምያ የሚታይ የማይታየው ዓለማቱ በእርሱ ተፈትሮዋል ነው ምክንያቱ የአዳምን እርቃን ሸፈነ ያን ሀፍረት ህይወት አለበሰው የፀጋውን ቁርበት የእባቡን እራስ ቀጥቅጦ የቀጣ በሴቲቱ ዘር ግንድ በስጋ የመጣ ከጥፋቱ ውሀ መርከብ የሚጠብቅ የማምለጫው መንገድ እንዲድን ፃድቅ በይስሀቅ ምትክ የታረደው በግ በበሩ መቃን ላይ የተረጨው ደም ነፍሴ በፍቅሩ ገመድ ታስረች፪ አየሱስ እየሱስ አለች ነውር የሌለበት ንፁህ መስዋት ጣፋጩ ሽታ በእግዚአብሔር ፊት የመስዋቱ በግ ሊቀ ካህኑ ስለኛ የሚታይ በመቅደሱ ከሰማይ ሰማያት የወረደው መና የፀናው አለት ያፈለቀው ውሀ የመውጫው መስላል ከምድር ወደ ስማይ የማህዘን እራስ ክቡር ህያው ድንጋይ የሁሉ ፊተኛ ጅማሬ ፍፃሜ የህይወት ምህራፍ ከፋች ደግሞም ድምዳሜ የፍጥረት እስትንፋስ ህልውና መሪ ፊተኛ ቀዳሚ የአለም ፈጣሪ ኢየሱስ ጥንትም የነበር ኢየሱስ ዛሬም ደግሞ ያለ ኢየሱስ ዘላለም የሚኖር ኢየሱስ ሁሌ እንደክበረ ከላይ ከአርያም ከክብር ዙፋኑ ከተንቆጠቆጠው ካማረው መንበሩ ወርዶ በኛ መሀል ድንኳኑን ተከለ ቃል ስጋ በመሆን በእኛ አደረ ከሀጢያት በስተቀር በሁሉ ያለፈ ሲኦልን ድል ነስቶ ሞትን ያሸነፈ መንግስቱ በምድር ሁሉ ሊጠቀልል ሊነግስ ዘላለም ተመልሶ ይመጣል ያለ የነበረ አልፋና ኦሜጋ አንዳች ፍትረት የለም ክብሩን የሚጥጋ ከስሞች የሚበልጥ ስምም ተስትቶታል ያልልክ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አድርጎታል ኢየሱስ ጥንትም የነበር ኢየሱስ ዛሬም ደግሞ ያለ ኢየሱስ ዘላለም የሚኖር ኢየሱስ ሁሌ እንደክበረ ነፍሴ በፍቅሩ ገመድ ታስረች በዐይኑዋ ማዳኑን አየች ነፍሴ በፍቅሩ ገመድ ታስረች አየሱስ እየሱስ አለች መስቀልህ በልቤ እንዲሳል ደምቆ ማንነህ እንዲታይ በእኔ ልቆ ይህ ጥማት በውስጤ ስርፆ ገባ እፋልግሀለውነጋ ጠባ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection