ባለብሰው ገላዬ አዲሱ ያረጃል የተጫሙ እግሮቼ ሌላ ያምራቸዋል። ደግሞ ይርበዋል ያበላሁት ሆዴ ጥሜ ቆረጠ ስል ውሃ ጠማው አፌ። የኑሮዬ ቋቱ ገደቡ ላይሞላ ስባክን ስዳክር ብዬ እንዳልቀር ኃላ ሰማዩን እረስቼ ምድሩን ቆንትጬ አብላኝ አጠጣኝ ስል ለስጋዬ ሮጬ። አይጠረቃ ህይወቴ አይሞላ ክፍተቴ መቼ በቃኝ ያውቃል ይሄ ማንነቴ። በምድራዊው አይደል በእህልና ውሃ ለካስ ኢየሱስ ነው የመንፈስ ፍስሀ ለካስ ኢየሱስ ነው የነፍሴ ፍስሀ። የልቤ ሀሴት የውስጤ እርካታ ኢየሱስ አንተ ነህ የነፍሴ ፋታ። በአንተ ደስ ይለኛል ሁልጊዜ ሀሴት አደርጋለው የሰጠኸኝ ደስታ ፍፁም ነው እፍለቀለቃለሁ በአንተ ደስ ይለኛል ሁልጊዜ ሀሴት አደርጋለው የሰጠኸኝ ተስፋ ፍፁም ነው እፈነድቃለሁ። ባልበላም ጠግቤ አድራለው ባልጠጣም እረክቼ እኖራለው አንተ ካለህ ምን እሆናለው? አንተ ካለህ ምን እሆናለው? በረሀው ላይ አስቀኸኛል ገነቴ ነህ አርክተኸኛል ፍቅርህ ብቻ ይበቃኛል መገኝትህ ያረካኛል አንተ ካለህ ምን ያሻኛል ፊትህ ብቻ ይበቃኛል።