በኃይለኛው ላይ ብርቱ ኃይለኛ በሚዳኘው ላይ ሲሰየም ዳኛ በዓለቃው ላይ አለ አለቃ የሰው ሹመቱ ልኩ ሲያበቃ ከፍ ካሉት በላይ ከፍ ብለህ በዙፋንህ ላይ የከበረ የታወቀ የገነነ ከሁሉ የላቀ ከሥም ሁሉ ሥመኛ አንተ እኮ ነህ ዝነኛ የለህ አቻ እኩያ የለህ ምትክ አምሳያ አዝ፦ አታይም ወደላይ የለህም የበላይ የሁሉ አለቃ ነህ የሁሉ ጌታ አታይም ወደላይ የለህም የበላይ የሁሉ ፈጣሪ ነህ የሁሉም መሪ ከላይ የመጣው ከሁሉ በላይ ነው እግዚአብሔር ካለልክ ከፍ ያደረገው እኛ ዝቅ ልንል እርሱ ግን ሊልቅ ነው የተገባው ነዉ ከሁሉ ሊበልጥ (2x) ኧረ ይህንን ጌታ ሊሽር ማንስ ሊረታ ሹመቱ ዙፋኑ ጽኑ ገደብ የለው ስልጣኑ አዝ፦ አታይም ወደላይ የለህም የበላይ የሁሉ አለቃ ነህ የሁሉ ጌታ አታይም ወደላይ የለህም የበላይ የሁሉ ፈጣሪ ነህ የሁሉ መሪ በሃይለኛው ላይ ብርቱ ሃይለእኛ በሚዳኘው ላይ ሲሰየም ዳኛ በዓለቃው ላይ አለ አለቃ የሰው ሹመቱ ልኩ ሲያበቃ ከፍ ካሉት በላይ ከፍ ብለህ በዙፋንህ ላይ የከበረ የታወቀ የገነነ ከሁሉ የላቀ ከስም ሁሉ ስመኛ አንተ እኮ ነህ ዝነኛ የለህ አቻ እኩያ የለህ ምትክ አምሳያ አዝ፦ አታይም ወደላይ የለህም የበላይ የሁሉ አለቃ ነህ የሁሉ ጌታ አታይም ወደላይ የለህም የበላይ የሁሉ ፈጣሪ ነህ የሁሉ መሪ በማስተዋል ከፍ ከፍ ያለ እራሱን አዋርዶ የከበረ በሰማይም በምድርም ክምድር በታችም የገነነ ምላስ ሁሉ ይመሰክራል ጉልበት ሁሉ ይንበረከካል ለእግዚአብሔር ልጅ ለኢየሱስ አለቅነት ተገብቶታል አዝ፦ አታይም ወደላይ የለህም የበላይ የሁሉ አለቃ ነህ የሁሉ ጌታ አታይም ወደላይ የለህም የበላይ የሁሉ ፈጣሪ ነህ የሁሉ መሪ