ብዙ እንቆቅልሽ እሄሄ ዛሬም ከብዶባቸው ዘወትር በልማድ ከበራፉ ደርሰው ይመጣሉ ይገባሉ ተቀምጠው ይወጣሉ ያመነ ሰው ሲድን ያዩ ምታስበኝ መች ነው ይላሉ ጌታ እንደሚችል አፋቸው ቢያወራ ልባቸው ቢፈተሽ አሄሄ ጥቂት እምነት የለም በጥርጣሬ እምነታቸው ጐሎ ሁሉን ቻዩ ጌታ ከእነርሱ ጋር ሆኖ ከነጥያቄያቸው ተመልሰው ሄዱ ትላንት የሚደክሙ አሃሄሄ ለአመታት በሃፍረት ከሰው ያገለላት ወዳጅ አልባ ሆና ብቻዋን ያስቀራት ለህመሟ መድሃኒት መፍትሄ ሲጠፋ በልቧ ስትጠብቅ ኢየሱስን በተስፋ ቀሚሱን በእምነት ብትነካ በእጆቿ እንደ እምነቷ ሆነ አዬ . (1) . የበሽታው ምንጭ ከስሩ ደረቀ በሰውነቷ ላይ . (2) . አዝ፦ (ለሚያምን) ኧረ ሁሉ ይቻላል (ለሚያምን) ቀሚሱ ያድናል (ለሚያምን) ቃሉ ይፈውሳል (ለሚያምን) ኢየሱስ ያድናል እምነት በመስማት ነው መስማትም በቃሉ እግዚአብሔርን ማወቅ ይበልጣል ከሁሉ ኤልሻዳይ ሁሉን ቻይ የሆነውን ጌታ እንዳይችል አሰብነው ሆነን በልብታ እግዚአብሔር እራሱ እንዲሆን ቢነግረን ማመን ይሳነናንል ከቃሉ ርቀን አዝ፦ (ለሚያምን) ኧረ ሁሉ ይቻላል (ለሚያምን) ቀሚሱ ያድናል (ለሚያምን) ቃሉ ይፈውሳል (ለሚያምን) ኢየሱስ ያድናል ባሪያዬ በጠና ታሞ ከቤቱ ላይ በቃልህ እዘዝ ብቻ ካልጋ ላይ ይነሳል ከጣሪያዬ በታች ልትገባ አይገባህም ተናገረኝ እንጂ ይህ ቀን አያልፈኝ ጌታም ተደነቀ በዚህ ሰው እምነት ብላቴናው ድኗል ሂድ ወደቤትህ አለው ኤልሻዳዩ ሁሉን የሚቻለው ቃሉን ሰደደና ባሪያውን ፈወሰው አዝ፦ (ለሚያምን) ኧረ ሁሉ ይቻላል (ለሚያምን) ቀሚሱ ያድናል (ለሚያምን) ቃሉ ይፈውሳል (ለሚያምን) ኢየሱስ ያድናል እምነት በመስማት ነው መስማትም በቃሉ እግዚአብሔርን ማወቅ ይበልጣል ከሁሉ ኤልሻዳይ ሁሉን ቻይ የሆነውን ጌታ እንዳይችል አሰብነው ሆነን በልብታ እግዚአብሔር እራሱ እንዲሆን ቢነግረን ማመን ይሳነናንል ከቃሉ ርቀን አዝ፦ (ለሚያምን) ጨለማው ይበራል (ለሚያምን) ብበሩ ይከፈታል (ለሚያምን) ተራራው ይናዳል (ለሚያምን) በእምነታችን ጌታ እንዴት ደስ ይለዋል