Song Lyrics

የሚረዳኝ

ፀሐይ አሽቆልቁላ በምዕራብ ስትጠልቅ ለምሽት ተረኛ ለጨረቃ ስትለቅ ጐኔን ላሳርፈው ከቀኑ ድካሜ ስተኛ እንቅልፌ ሲያደርሰኝ በህልሜ ህልሜ ቅዥእት ሆኖ ጨለማው በርትቶ እጥፍ ሲሆን ሌቱ ሲረዝም ምሽቱ አቤቱ ወደአንተ ድምጼን አሰማለሁ ፈጥነህ እንደትመጣ እለምንሃለሁ አዝ፦ የሚረዳኝ የለምና ከጐኔ አትራቅ የሚያግዘኝ የለምና ከጐኔ አትራቅ ፀጥ ረጭ ባለው ሰዓት ኮቴ በሌለበት ሁሉ ቤቱ ከቶት እፎይ በሚልበት ሃሳቤን ሚጋራ ጆሮ የሚሰጠኝ ሲጠፋ ከጐኔ ጭንቄን ሚካፈለኝ የሕይወቴ ብርሃን በጽልመት ሲሞላ የልቤ ትርታ በሃይል ሲመታ አቤቱ ወደአንተ ድምጼን አሰማለሁ ፈጥነህ እንድትመጣ እለምንሃለሁ አዝ፦ የሚረዳኝ የለምና ከጐኔ አትራቅ የሚያግዘኝ የለምና ከጐኔ አትራቅ ድንጋይ ተንተርሶ ያንቀላፋው ያዕቆብ መልካም ራዕይ አይቶ ተስፋው ሲያብብ የቀድሞው ታሪኩን ሥሙን ለውጠኀው የብዙዎች አባት እስራኤል ነህ አልከው ጭኑ የተነካ እግሩ የሚያነክስ ሁለት ሰራዊት ነው ነግቶለት ሲመለስ ልታድነኝ ብትወድ ፈጥነህ ጐህ ሳይቀድ ሊነጋ አያቅላላ ወደ እኔ ሳትመጣ አዝ፦ የሚረዳኝ የለምና ከጐኔ አትራቅ (ከጐኔ) የሚያግዘኝ የለምና ከጐኔ አትራቅ (2x) አትራቅ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection