Song Lyrics

ዋጋ ስጠው

ዛሬ ታይቶ ነገ ሊጠፋ ድንገት ሊሰበር እንደሸክላ ላጭሩ ዘመኔ ቀጠልኩለት ዕድሜ መላ ዘይጃለሁ እፎይ ትበል ነፍሴ አዝ፦ ለሕይወቴ ዋጋ ሰጠሁ ኢየሱስን ማግኘቴ ከሞት ወዲያ እሻገር ዘንድ ላልሞት ሕያው ሆኜ ሰረገላው አሳፈረኝ ሊያሻግረኝ ማዶ ጠርቶኝ ኢየሱስ ወደ እረፍቱ እንዳልጠፋ ወዶ (2x) ሞት እንደው አይቀርም ሰው ግን ሞት ይፈራል ከበሩ ላይ ደርሶ ሊወስደው ሲመጣ በእምባ ዐይኑ አይቶታል ነፍሱን ይወስዳታል ድምጹን ሳያሰማ ላይመልሰው ዳግም አንዴም ሳያቅማማ ነፍሱን ይወስዳታል ኮቴ ሳያሰማ ላይመልሰው ዳግም አንዴም ሳያቅማማ በድኑን ታቅፈው ወዳጅ ዘመዶቹ ቢያለቅሱ አይመለስ ደረት እየደቁ በእርግጥ በኢየሱስ አምኖ ካልዳነ ሰው ዋይ ዋይ ይበሉለት ደግመው ያልቅሱለት ግን በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ ከዳነ ሰው እልል ይበሉለት ለቅሷቸውን ትተው አዝ፦ ለሕይወቴ ዋጋ ሰጠሁ ኢየሱስን ማግኘቴ ከሞት ወዲያ እሻገር ዘንድ ላልሞት ሕያው ሆኜ ሰረገላው አሳፈረኝ ሊያሻግረኝ ማዶ ጠርቶኝ ኢየሱስ ወደ እረፍቱ እንዳልጠፋ ወዶ (2x) ከንቱ ለሆነ ነገር ታይቶ ለሚጠፋ ለሕይወት ዋስትና አጥተህ ወንድሜ አትልፋ ክርስቶስን አምነህ ዋጋ ስጥ ለሕይወትህ ታይቶ የሚጠፋ እንዳያታልልህ ነይ እህቴ ና ወንድሜ ዘመኑ አልቋል ዛሬ ነገ አትበል የመዳን ቀን ዛሬ ነው እንዳትወላውል ከጨለማ ከሞት ከሞት አምልጥ እሩጥ ኢየሱስ ያድናል ለሕይወትህ ዋጋ ስጥ የመዳንህ ቀን ዛሬ ነው እባክህ ወገኔ አትወላውል አትባክን ትረፍ ከኩነኔ (2x) ትረፍ ከኩነኔ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection