Song Lyrics

ከአፌ አላወርድም

አዝ፦ ኢየሱስ ኢየሱስ ወዳጄ ኢየሱስ ኢየሱስ መድሃኒቴ ከአፌ አላወርድም ይህን ሥስምክን አላርፍም አልረካም እስካገኝህ (2x) ውኃ በማጣት እንደደረቀ መሬት አግኝታ እስክትረካ ነፍሴ እያት ስትዋትት ሃይልና ሞገስህ በሞላው መቅደስህ ፍቀድልኝና ልየው ያን ፊትህን እንጨትና ውኃ በሌለበት ቦታ እኔ ግን እሄዳለሁ ውድዬን ፍለጋ አንድ ጊዜ ብቻ አስበኝ መድህኔ ጠግቤ እኖራለሁ በሕይወት ዘመኔ አንድ ጊዜ ብቻ አስበኝ ሬድኤቴ ፍቅርህ መድሃኒት ነው ፈውስ ለሕይወቴ አዝ፦ ኢየሱስ ኢየሱስ ወዳጄ ኢየሱስ ኢየሱስ መድሃኒቴ ከአፌ አላወርድም ይህን ሥምክን አላርፍም አልረካም እስካገኝህ (2x) የተመኘሁትን ያሰብኩትን ይዤ ግን አልረካሁኝም አለሁኝ ተክዤ ጐተራዬ አልሞላም ፍላጐቴ አልቆመ የውስጠቴን ርሃብ ይሄ አላተገበም ወደ አንተ እጠራለሁ ሙጥኝ እልሃለሁ ያገኘሁህ እለታ እንዴት እሆናለሁ ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንዲጠግብ ነፍሴ ትጠግባለኝ በክብርህ በግርማህ ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንዲጠግብ ነፍሴ ትጠግባለኝ ጌታዋን ስታስብ ኢየሱስ የሕይወቴ ፍሰሃ ኢየሱስ ብኖር በበረሃ ኢየሱስ የሕይወቴ ብርሃን ኢየሱስ ባልፍም በጨለማ አንድ ጊዜ ብቻ አስበኝ ሬድኤቴ ፍቅርህ መድሃኒት ነው ፈውስ ለሕይወቴ አንድ ጊዜ ብቻ አስበኝ መድህኔ ጠግቤ እኖራለሁ በሕይወት ዘመኔ በመጠበቂያዬ በማማዬ ሆኜ እጠብቅሃለሁ እንዳይህ አምኜ ዝለቴ ድካሜ ይወገድ አፍረቴ በሰፈሬ እንድታልፍ እንድትገባ ቤቴ ባላሰብኩት ሰዓት ባልጠበኩት ቦታ በጊዜ ሰሌዳ በአንተ አቆጣጠር የጠበኩህ ጌታ ድንገት ትመጣለህ ረሃቤን ጥማቴን ያኔ ታረካለህ የጠበኩህ ጌታ ድንገት ትመጣለህ ረሃቤን ጥማቴን አንተው ታረካለህ አዝ፦ ኢየሱስ ኢየሱስ ወዳጄ ኢየሱስ ኢየሱስ መድሃኒቴ ከአፌ አላወርድም ይህን ሥምክን አላርፍም አልረካም እስካገኝህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection