Song Lyrics

አውቃለሁ

ግራና ቀኜን ከፊት ከኋላ ሲጨልምብኝ ባጣ ማረፊያ ተስፋዬ ያልኩህ በእጄ ይዤ ድንገት ሲከዳኝ ብቀር ተክዤ የተውከኝ ሲመስለኝ አምላኬ ከላይ ምድር ጐርብጣ ቢዘጋ ሰማይ አሃሃ አውቃለሁ አንተ ሁልጊዜ ትክክል እንደሆንክ አውቃለሁ ተናግረህ ማትፈጽም ቀላባይ እንዳልሆንክ አዝ፦ አውቃለሁ ለእኔ መልካም ሃሳብ እንዳለህ ፍቅር ነው አላማህ በእኔ ላይ ውዴ ፍቅር ነው አላማህ በእኔ ላይ ውዴ (2x) ሀጥያቴ ሲጋለጥ ለአሉታ ወሬ በነበር ሆኖ ሳይቀር ነገሬ የሽንፈት ቃላት ከአፌ እንዲወጣ ሲወተውተኝ ምክንያት ቢያጣ ሙሾ ሲደረድር ይኸው ጠፋሁ ብዬ በገናዬን ስጥል ሊስቅ ባላንጣዬ አሃሃ አውቃለሁ ዞርበል አንተ ክፉ ብሩህ ቀን አያለሁ አሃሃ አውቃለሁ እግዚአብሔር ጻዲቅ ነው አመሰግናለሁ አዝ፦ አውቃለሁ ለእኔ መልካም ሃሳብ እንዳለህ ፍቅር ነው አላማህ በእኔ ላይ ውዴ ፍቅር ነው አላማህ በእኔ ላይ ውዴ (2x) ልዩ ነህ ፍቅር ነህ በእኔ ላይ አላማህ ልዩ ነው ልዩ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection