አዝ፦ ነፍሴ ሆይ ዘምሪ ለወደደሽ ጌታ አንቺን ከገሃነም ከሲኦል ላወጣ እስኪ ድምጽሽን አሰሚ ኢየሱስ ያድናል እያልሽ ዘምሪ ኢየሱስ በፍቅሩ ወዶሻል ሞትን ድል አድርጐ ከአብ አስታርቆሻል ታዲያ ለምን እረሳሽው ይህንን ውለታ ዘምሪለት እንጂከጥዋት እስከ ማታ አዝ፦ ነፍሴ ሆይ ዘምሪ ለወደደሽ ጌታ አንቺን ከገሃነም ከሲኦል ላወጣ እስኪ ድምጽሽን አሰሚ ኢየሱስ ያድናል እያልሽ ዘምሪ ሞትና መውጊያውን ሰባብሮ አንችን ግን መርጦሻል ጠላትን አባሮ አትቆጥቢ ተናገሪ የምስራቹን ቃል ላመኑት ሁሉ መጠጊያ ይሆናል አዝ፦ ነፍሴ ሆይ ዘምሪ ለወደደሽ ጌታ አንቺን ከገሃነም ከሲኦል ላወጣ እስኪ ድምጽሽን አሰሚ ኢየሱስ ያድናል እያልሽ ዘምሪ ነፍሴ ሆይ በእግዚአብሔር ታመኚ ባለውለታሽን እርሱን አመስግኝ ምህረቱ ለዘላለም አቁሞሻልና ማዳኑ ይነገር ዛሬም እንደገና አዝ፦ ነፍሴ ሆይ ዘምሪ ለወደደሽ ጌታ አንቺን ከገሃነም ከሲኦል ላወጣ እስኪ ድምጽሽን አሰሚ ኢየሱስ ያድናል እያልሽ ዘምሪ