የዘለዓለም መኖሪያዬ አንተ እኮ ነህ ማረፊያዬ ታምኘብህ አላፈርኩም በምድረበዳ አልቀረሁም አዝ፦ ትልቅ ያየሁት አንተን ብቻ በምድር በሰማይ የለህ አቻ እግዚአብሔር አንተ እግዚአብሔር ነህ ከአማልክት ሁሉ ትለያለህ (2x) ካየሁት ሁሉ ትበልጣለህ በክንዶችህ አየተደገፍኩ አቤት ባንተ ስንቱን አለፍኩ ማዳንህን አይቻለሁ ስለውለታህ እዝምራለሁ አዝ፦ ትልቅ ያየሁት አንተን ብቻ በምድር በሰማይ የለህ አቻ እግዚአብሔር አንተ እግዚአብሔር ነህ ከአማልክት ሁሉ ትለያለህ (2x) ካየሁት ሁሉ ትበልጣለህ የዚህ ዓለም ጠቢባኖች የምድር ላይ ኃያላኖች ሁሉም ወድቀው ተረስተዋል አንተ ብቻ ያው ነህ ተከብረሃል አዝ፦ ትልቅ ያየሁት አንተን ብቻ በምድር በሰማይ የለህ አቻ እግዚአብሔር አንተ እግዚአብሔር ነህ ከአማልክት ሁሉ ትለያለህ (2x) ካየሁት ሁሉ ትበልጣለህ