አዝ፦ መውጣትህ መግባትህ በእግዚአብሔር እጅ ነው ታዲያ የምትፈራው ምትሰጋው ምንድነው የሚያሰጋህ ታዲያ የቱ ነው (2x) በሁሉም ላይ ጌታ የበላይ ነው (2x) ዙሪያህ የከበበህ ሁኔታ የማይሆን ቢመስልህ የምታየው ሁሉ ቢዘጋ ግራ ቢገባህም የምትፈራው ነገር ላይወርስህ አይዞህ ኢየሱስ አለልህ አዝ፦ መውጣትህ መግባትህ በእግዚአብሔር እጅ ነው ታዲያ የምትፈራው ምትሰጋው ምንድነው የሚያሰጋህ ታዲያ የቱ ነው (2x) በሁሉም ላይ ጌታ የበላይ ነው (2x) ሰበሰብኩኝ ስትል ያያዝከውከእጅህ ቢበተንም ተስፋ ያረከው ሁሉ እርቆ አልያዝ ቢልህም በእግዚአብሔር ሀሳብ ላይ ኑር እንጂ አይዞህ አለህ ወዳጅ አዝ፦ መውጣትህ መግባትህ በእግዚአብሔር እጅ ነው ታዲያ የምትፈራው ምትሰጋው ምንድነው የሚያሰጋህ ታዲያ የቱ ነው (2x) በሁሉም ላይ ጌታ የበላይ ነው (2x) አልጥልህም ብሎ የጠራህ እግዚአብሔር ታማኝ ነው ላንተ ባይመስልህም አላማው ሁሉ ለበጐ ነው ሳትፈራ ጥቂት ታገሰው ጽና ማጉረምረሙን ተወው አዝ፦ መውጣትህ መግባትህ በእግዚአብሔር እጅ ነው ታዲያ የምትፈራው ምትሰጋው ምንድነው የሚያሰጋህ ታዲያ የቱ ነው (2x) በሁሉም ላይ ጌታ የበላይ ነው (2x)