Song Lyrics

አለኝ

Ephrem Dagne
Alayim Wedehuala
አለኝ እኔስ አለኝ ብዬ ምታመነው ዘመን የማይሽረው ለእኔስ ኢየሱስ ነው ሁሉ ሙሉ ሆኖ እጥፍ ቢኖረንም ለነፍሴ ጠበቃ ዋስ አይሆንልኝም ለኔ አለኝ የምለው ሁሉ የማመልከው አልፋማ ኦሜጋ ትልቅ ኢየሱስ ነው አዝ፦ አለልኝ የምለው ለእኔስ ኢየሱስ ነው (2x) ዝና ከበሬታ በዚህ በምድር ነው አንድ ቀን ሲያበቃ ሁሉም አላፊ ነው በሰማይ ቢሆን ደግሞምበምድር ለኔስ ድጋፍ አለኝ የማይሰበር አዝ፦ አለልኝ የምለው ለእኔስ ኢየሱስ ነው (2x) ሰው ከማይገምተው ካልታሰበ ስፍራ በፍቅሩ ማረከኝ ክብሩን እንዳወራ ከሳሾቹን ሁሉ እያሳፈረልኝ አዲስን ዝማሬ በአፌ ጨመረልኝ አዝ፦ አለልኝ የምለው ለእኔስ ኢየሱስ ነው (2x) ለሰይጣን ሽንገላ ጆሮዬን አልሰጥም ቢያወራ ቢያወራ ተስፋዬን አልጥልም ቢጐድልም ቢሞላ ጌታን አመልካለሁ ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ እርሱን እግኝቻለሁ አዝ፦ አለልኝ የምለው ለእኔስ ኢየሱስ ነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection