አዝ፦ አላፈርኩም አንተን ብዬ (2x) ዛሬም አለሁኝ ተደላድዬ ከዚህ ዓለም ክፋት ፍቅርህ ለይቶኛል የምህረትህ ብዛት ቤትህ አኑሮኛል ታዲያከበርኩ እንጂ መች ከሰርኩኝ እኔ የዘላለም አምላክ እያለ ከጐኔ (4x) ኢየሱስ አለ ከጐኔ አዝ፦ አላፈርኩም አንተን ብዬ (2x) ዛሬም አለሁኝ ተደላድዬ ጠላት በእኔ ላይ በተነሳ ጊዜ ነፍሴን ሊያስፈራራ ከቦኝ በትካዜ ኢየሱስ ደረስህልኝ አሳርፈኽኛል ስምህ ጋሻ ሆኖ አስመልጠኸኛል (4x) ዛሬ አድርሰኸኛል አዝ፦ አላፈርኩም አንተን ብዬ (2x) ዛሬም አለሁኝ ተደላድዬ ድንቅ ታምራትህን ማዳንህን እያየሁ ቃል ኪዳን አለብኝ አገለግላለሁ ገና የሚበልጥ አዲስ ክብር አለ ዛሬ ዓይኔ ከሚያየው ከዚህ የተሻለ (4x) ሌላ ክብር አለ አዝ፦ አላፈርኩም አንተን ብዬ (2x) ዛሬም አለሁኝ ተደላድዬ