Song Lyrics

ተማምኜ

Ephrem Dagne
Alayim Wedehuala
ላመስግን የኔጌታ ላመስግን ላመስግን ደጋግሜ ላመስግን በጠላቴ ሰፍር እሮሮ ሲሰማ ለእኔ ግን በዛልኝ የምሥጋና ዜማ ከፊቴ የቆመው ትልቁ ተራራ ደልዳላ ሆነልኝ ስምህን ስጠራ ከፊቴ የቆመው ትልቁ ተራራ ደልዳላ ሆነልኝ ስምህን ስጠራ አዝ፦ ተማምኜ እኖራለሁ ተማምኜ (2x) በዘላለሙ ክንድህ በቅፍህ ታምኜ አልጥልህም ብለህ በፍቅርህ ጠርተኽኝ ፀጋን አለበስከኝ በሄድኩበት ሁሉ ተከናወነልኝ ሞገስ ሆነህልኝ እንድም ነገር የለም ከኔ ነው የምለው የኔ ነው የምለው ሁሉም ያማረልኝ ኢየሱስ ባንተ ነው ጌታዬ ባንተ ነው አዝ፦ ተማምኜ እኖራለሁ ተማምኜ (2x) በዘላለሙ ክንድህ በቅፍህ ታምኜ ውድቀቴን በሚሻው በጠላቴ ላይ (2x) ከፍ ከፍ አረከኝ ክብርህ እንዲታይ (2x) ልቤ በማዳንህ እየተደነቀ (2x) ለታላቅነትህ ዜማን አፈለቀ (2x) አዝ፦ ተማምኜ እኖራለሁ ተማምኜ (2x) በዘላለሙ ክንድህ በቅፍህ ታምኜ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection