Song Lyrics

አላይም የኋላ

Ephrem Dagne
Alayim Wedehuala
አዝ፦ እግዚአብሔር አዋቂ ነው (2x) ያለውን ሊፈጽም ለሁሉም ጊዜ አለው ለአንተም ጊዜ አለው ለአንቺም ጊዜ አለው ለእኔም ጊዜ አለው ለሁሉም ጊዜ አለው በሰማይ የሚታይ ደመና ባይኖርም ንፋስም ባይኖርም አይዘንብም አልልም የተናገረኝን አልጠረጥረውም (2x) እርሱ ይሆናል ካለ አይሆንም አልልም አዝ፦ እግዚአብሔር አዋቂ ነው (2x) ያለውን ሊፈጽም ለሁሉም ጊዜ አለው ለአንተም ጊዜ አለው ለአንቺም ጊዜ አለው ለእኔም ጊዜ አለው ለሁሉም ጊዜ አለው አላሳልፍ ብሎ ዮርዳኖስ ቢሞላ ጉልበቴን ሊያላላ አላይም የኋላ የጠራኝን አምላክ ቃሉን አምነዋለሁ እታመነዋለሁ በእምነት ተሻግሬ በድል እቆማለሁ አዝ፦ እግዚአብሔር አዋቂ ነው (2x) ያለውን ሊፈጽም ለሁሉም ጊዜ አለው ለአንተም ጊዜ አለው ለአንቺም ጊዜ አለው ለእኔም ጊዜ አለው ለሁሉም ጊዜ አለው በጉልበቱ ጽናት የሚራመደው (2x) አምላኬ እርሱ ነው ከፍ ከፍ ቢያደርግ ሲያሻው ቢከለክል (2x) በሚሰራው ሁሉ እግዚአብሔር ትክክል (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር አዋቂ ነው (2x) ያለውን ሊፈጽም ለሁሉም ጊዜ አለው ለአንተም ጊዜ አለው ለአንቺም ጊዜ አለው ለእኔም ጊዜ አለው ለሁሉም ጊዜ አለው አምላክህ ትቶሃል ጠላቴ ቢለኝም ቢነዘንዘኝም ይህ ለኔ አይገባኝም ምንም ቀን ቢገፋ ተስፋው ቢዘገይም አምላኬ ያለው ቃል መፈጸሙ አይቀርም አዝ፦ እግዚአብሔር አዋቂ ነው (2x) ያለውን ሊፈጽም ለሁሉም ጊዜ አለው ለአንተም ጊዜ አለው ለአንቺም ጊዜ አለው ለእኔም ጊዜ አለው ለሁሉም ጊዜ አለው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection