አዝ፦ አንተ ይሁን ስትል የማይሆን ምን አለ (2x) ቃል ተናገር እንጂ የማይሆን ምን አለ (2x) ጊዜ የማይሽረው ባለበት የሚገኝ እንዳንተ አላይሁም እንደቃሉ ታማኝ አቤት የእኔ ጌታ ስራህ ያስገርማል ሰማይና ምድርን በቃልህ ሰርተሃል በመገዛት ያድራል ፍጥረት በሥልጣንህ ታስተዳድራለህ የለም የሚያቅትህ አዝ፦ አንተ ይሁን ስትል የማይሆን ምን አለ (2x) ቃል ተናገር እንጂ የማይሆን ምን አለ (2x) ጊዜ የማይሽረው ባለበት የሚገኝ እንዳንተ አላይሁም እንደቃሉ ታማኝ ይሁን ያልከው ሁሉ መፈጸሙ ላይቀር የሰው ላይ ታች ማለት ምንድነው መሸበር እኔስ ለፈቃድህ ራሴን ሰጥቻለሁ አንተ ያልከው ይሁን እገዛልሃለሁ አዝ፦ አንተ ይሁን ስትል የማይሆን ምን አለ (2x) ቃል ተናገር እንጂ የማይሆን ምን አለ (2x) ጊዜ የማይሽረው ባለበት የሚገኝ እንዳንተ አላይሁም እንደቃሉ ታማኝ ምንም በሌለበት በምድረበዳው ታማኝነትህን አይቻለሁ ዛሬም ክንደ ብርቱ ገናና ነህና ያልከው ሁሉ ይሆናል ሀይል ያንተ ነውና አዝ፦ አንተ ይሁን ስትል የማይሆን ምን አለ (2x) ቃል ተናገር እንጂ የማይሆን ምን አለ (2x) ጊዜ የማይሽረው ባለበት የሚገኝ እንዳንተ አላይሁም እንደቃሉ ታማኝ