Song Lyrics

ለምልሟል

Ephrem Dagne
Alayim Wedehuala
አዝ፦ ምድረ በዳዬ ለምልሟል (2x) ኢየሱስ ዋጋ ከፍሎልኛል የዘላለም ኪዳን ገብቶልኛል የማይሻር ኪዳን ገብቶልኛል በልቤ ሲገባ የየሱሴ ፍቅሩ ሕይወቴ ተገዛ ጨከነ ለፍቅሩ ዛሬ በደስታ በአደባባይ ቆሜ ያድናል እላለሁ ደግሜ ደግሜ ኢየሱስ ጠበቃ ሆኖልኛል ከእንግዲህ የትኛው ያሰጋኛል ዛሬ ምን ይዋጠው ያክፉ ጠላቴ በጌታ በኢየሱስ ሙሉ ነው ሕይወቴ ምክንያትን ፈላልጐ ዙሪያዬን ቢዞረው እኔ እንደው አልገኝ አጥሬ ኢየሱስ ነው ኢየሱስ ጠበቃ ሆኖልኛል ከእንግዲህ የትኛው ያሰጋኛል ሞትን ድል አድርጐ በተነሳው ጌታ እኔስ ተፈወስኩኝ ከሃጥያት በሽታ ዓለም ሰይጣን ሥጋ ዳግም ላያገኙኝ በጌታ በኢየሱስ ከሞት አመለጥኩኝ ኢየሱስ ጠበቃ ሆኖልኛል ከእንግዲህ የትኛው ያሰጋኛል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection