ነሁሽጣር ብዬ ሰብሬዋለሁ ያስጨነቀኝን ረግጨዋለው ተራራ መዞር አበቃ ዛሬ ዝማሬ ሆኗል አዲስ ዝማሬ አዝ:- አዲስ ዝማሬ አዲስ ዝማሬ (2x) አላሳልፍ ያለው ከፊቴ የቆመው ጌታዬ ሲመጣ ገለል አደረገው ቀድሞኝ እግዚአብሔር ከፊቴ ሲወጣ ጠላቶቼ ሁሉ በነኑ እንደ ጤዛ አዝ:- አዲስ ዝማሬ አዲስ ዝማሬ (2x) የኤልያስ አምላክ በእሳት የመለሰው ዛሬም በእኔ ዘመን የእኔም ጌታ ነው እንኳን ማንነቱ ስሙ ኃይለኛ ነው ጠላቴን ገጥሜ እበቀለዋለሁ ሥሙ የኤልያስ አምላክ ሥሙ የተባለዉ ሥሙ በእኔም ዘመን ሥሙ ኃይለኛ ነው (2x) ሰይጣን ወደቀ እንደመብረቅ ስልቱ ገብቶኛል የመዋጋት አልጨነቅም ለተሸነፈ ከእግሬ በታች ነው ስፍራው ታወቀ አዝ:- አዲስ ዝማሬ አዲስ ዝማሬ (2x) አላሳልፍ ያለው ከፊቴ የቆመው ጌታዬ ሲመጣ ገለል አደረገው ቀድሞኝ እግዚአብሔር ከፊቴ ሲወጣ ጠላቶቼ ሁሉ በነኑ እንደ ጤዛ አዝ:- አዲስ ዝማሬ አዲስ ዝማሬ (2x) የኢናቅ ልጆች ረጃጅሞቹ በአይን ሲታዩ አስፈሪዎቹ በእግዚአብሔር መንፈስ ሆነው ሳያቸው ለካስ እንደ እንጀራ ሚበሉ ናቸዉ አዝ:- አዲስ ዝማሬ አዲስ ዝማሬ (2x)