Song Lyrics

የፍቅር አምላክ

Yefiqir Amlak

Ephrem Alemu
Yenefsie Mamlecha
አባብዬ ሳልውድህ ወደኸኝ ሳልመርጥህ መርጠኸኝ በእየሱሴ የዘላለም ህይወት በነፃ ሰጠኸኝ እድለኛ እድለኝ ነኝ/4 የፍቅር አምላክ የፍቅር ጌታ ልጁን ገለጠው በኔ ሁኔታ እሱን ለማምለክ ማንስ ተው ቢለኝ የእየሱስ ፍቅር ውስጤ ገብቶብኝ በዋጋ ገዝቶኛል ሃሌሉያ የራሴ አይደለሁም እርሱም የኔ ሆኗል ማንም አይለየኝም በእጆቹ መዳፍ ሃሌሉያ እየሱስ ቀርፆኛል ታዲያ ከዚ ፍቅር ማንስ ይለየኛል የፍቅር አይኑ አልተለየኝም እባቡ ጊንጡ አልነደፈኝም ይልቅ ከፍ ከፍ ከፍ አደረገኝ በጠላቴ ፊት በዘይት ቀባኝ የሰላሙ ንጉስ ሃሌሉያ በቤቴ ገባና ሃሌሉያ በከፍታ አቆመኝ ዳግም ለምስጋና የሚያስፈራኝ የለም ከእንግዲ በኋላ ጌታ ጎኔ ቆሟል በፊቴም በኋላ ምህረቱ ገኖ ባይኔ አይቻለው እየሱስዬ እወደዋለው አይረሳኝም የፍቅሩ ስራ በቀራንዮ በዛ ተራራ በመስቀል ላይ ሆኖ ሃሌሉያ ስለኔ አልቅሶ አድኖኛል ጌታ እዳዬን ሰርዞ በመስቀል ላይ ሆኖ ሃሌሉያ ስለኔ አልቅሶ አድኖኛል ጌታ እዳዬን ሰርዞ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection