ያምላኬ ጉዳይ ከበደብኝ ቅጥሩ ፈርሶ ስላየሁኝ ልቤን ላስታመው ደግሞ ምግብ አልበላ ቅጥሩ ታድሶ ካላየሁማ ኧኸ ጦቢያው ሰምበላት ኧኸ ውረድ ሲሉኝ ቅጥር ልሰራ ሄጃለሁኝ (2x) ና ውረድ ሲሉኝ (3x) ስፍራው ተመችቶኝ እዛው ቀረሁኝ አልወርድም አልወርድም ከተራራው ላይ የእግዚአብሔርን ክብር በዓይኖቼ እስከማይ አልዛቤል ምድሩን ሃገሩን ገዝታ ምን ሰላም አለ ለእኛ መኝታ እረፍት የለኝም ለሽፋሽፍቴ እስካያት ድረስ ወድቃ ከፊቴ ኧኸ ውሻ ሲበላት ኧኸ በዓይኔ አያለሁ የትናገረኝ ጌታ ታማኝ ነው (2x) ና ውረድ ሲሉኝ (3x) ስፍራው ተመችቶኝ እዛው ቀረሁኝ አልወርድም አልወርድም ተራራው ላይ የእግዚአብሔርን ክብር በዓይኖቼ እስከማይ ቤቱ በሸቀጥ ነጋዴ ሞልቶ አጠራው ጌታ ጅራፍን ሰርቶ ሁሉም ይሰግዳል ለአብ ክብር ቤቱ ሲጠራ የእግዚአብሔር ኧኸ የቤቱ ቅናት ኧኸ እኔን በልቶኛል ቤቱ ሲጠራ በዓይኔ ያሳየናል (2x)