አዝ:- አይጥልም አይረሳም አይጥልም አይረሳም (2x) ሰው ማድረግ ይችላል አይጥልም አይረሳም ከአመድ ላይ ያነሳል አይጥልም አይረሳም (2x) አቅም ጉልበት አጣሁ ብሎ በፍራቻ ለሚያለቅሰው ሰው የሌለው የተረሳ እምባው ምግቡ የሆነ ሰው ተስፋው ድሉ ጨልሞበት የሞቱን ቀን ለጠበቀው ዛሬ በቃ የለቅሶ ቀን እግዚአብሔር ሲጐበኘው (2x) አዝ:- አይጥልም አይረሳም አይጥልም አይረሳም (2x) ሰው ማድረግ ይችላል አይጥልም አይረሳም ከአመድ ላይ ያነሳል አይጥልም አይረሳም (2x) በመንፈቀ ሌሊት ቀሰቀሰኝ ዘምር ብሎ አዶናይ ኢየሱስ ነው ይክበር በዝማሬ በዓለም ላይ የሌለ ሚስጥረኛ ታማኝ ትጉ ደግ እረኛ ኢየሱስ ነዉ የልቤ እረኛ (2x) ቀን ሲከፋ ስጨላልም አይዞህ የሚል ወዳጅ የለም በደህና ቀን የነበረው በክፉ ቀን ምን ወሰደዉ የእኔስ አባት ለየት ይላል በመከራ ቀን ይደርሳል እርሱን ታምኖ ለሚጣራ ከተፍ ይላል የሚያኮራ (2x) እኔን ያከበሩ ይከብራሉ የናቁኝም ይናቃሉ ብሏልና አባቴ በቃሉ እሱን ላከበረው ለታመነው በመንገዱ ለሚጓዘው ከቶ አየውድቅም ጠንካራ ግንብ አለው አዝ:- አይጥልም አይረሳም አይጥልም አይረሳም (2x) ሰው ማድረግ ይችላል አይጥልም አይረሳም ከአመድ ላይ ያነሳል አይጥልም አይረሳም (2x)