Song Lyrics

አንደኛዬ

“አንደኛዬ ነህ ኢየሱሴ አንደኛዬ ለእኔ አንደኛዬ ነህ ኢየሱሴ በፍቅር ምርጫዬ” አንደኛዬ ነህ ኢየሱሴ አንደኛዬ ለእኔ አንደኛዬ ነህ ኢየሱሴ በፍቅር ምርጫዬ (2x) የአንተን በብዙ ሺህ ፍቅርህን ስላየሁ እኔስ ከሰው ልጅ ይለያል እላለሁ እልፍ አንደበት ኖሮኝ ስላንተ ባወራ ከቶ አይሰለቸንም ብዘምር የእንተን ሥራ የአንተንስ ፍቅር ዘምሬ አልጨርስ የአንተንስ ውለታ አልረሳውም ለአፍታ (2x) ያልሆነልኝ ምን አለ ያልሰጠኝስ ምን አለ ያልዋለልኝ ምን አለ ፍቅር ነው ተባለ ዛሬም አንደኛ ኢየሱስ የኛ ነገም አንደኛ ኢየሱስ የኛ ሁሌም አንደኛ ኢየሱስ የኛ (አንደኛ) ይባል አንደኛ (ይባል አንደኛ) ኢየሱስ የኛ እኔስ በላዬ ላይ ንጉሴን ሾሜያለሁ አምናና ካቻምናን ያለፍኩት በእርሱ ነዉ መቀነት በወገብ እንደሚጠብቀው እኔስ ከኢየሱስ ጋር ተጣብቄያለሁ ያንተንስ ፍቅር ዘምሬ አልጨርስ ያንተንስ ውለታ አልረሳውም ለእፍታ (2x) ያልሆነልኝ ምን አለ ያልሰጠኝስ ምን አለ ያልዋለልኝ ምን አለ ፍቅር ነው ተባለ አንደኛዬ ነህ ኢየሱሴ አንደኛዬ ለኔ አንደኛዬ ነህ ኢየሱሴ በፍቅር ምርጫዬ (2x) በመስቀሉ ሥራህ በአራፔ ፍቅርህ ወደኸኛል ጌታ የኔ ወግ የኔ ክብር ኪዳን ገብቶልናል አልጥልህም ብሎ ዛሬም ይዘምራል አንደኛ ተብሎ አንደኛዬ ነህ ኢየሱሴ (አንደኛ) አንደኛዬ ለእኔ አንደኛዬ ነህ ኢየሱሴ (ለእኔ አንደኛዬ) በፍቅር ምርጫዬ ዛሬም አንደኛ ኢየሱስ የእኛ ነገም አንደኛ ኢየሱስ የእኛ ሁሌም አንደኛ ኢየሱስ የእኛ ይባል አንደኛ ኢየሱስ የእኛ አንደኛዬ ነህ ኢየሱሴ (ለኔ አንደኛዬ) አንደኛዬ ለኔ (አንደኛ) አንደኛዬ ነህ ኢየሱሴ በፍቅር ምርጫዬ (ለእኔ) (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection