Song Lyrics

ኩራቴ

ቆይቷል ከገባኝ እውነቱ ወንጌል እንደሆነ መድሃኒቱ ሌላ ሌላ ማየት ትቻለሁ ኢየሱስ ያድናል ብያለሁ (2x) ሌላ ሌላ ትቻለሁ ጌታ ጌታን ብያለሁ (2x) የዓለም ትርምስ ስላልተመቸኝ ወደ ጌታ ፊቴን አዙርያለሁኝ ጌታ ጌታን ማለት ያዋጣኛልና አምላኬን ልማጸን መቅደሱ ልግባና አዝ:-ለዚህ ነው ኩራት ስላለኝ አባት ለዚህ ነው ትምክቴ ስላለኝ አባት አባት ስላለኝ አባት (2x) ዓይኖቼ ተከፍተው ብድራቴን ሳይ በእምነት እምብ አልኩኝ መሾም ግብጽ ላይ የልጅ ልጅ ከመባል ከፈርኦን ጮማ መከራን መረጥኩን ከእርሱ ሕዝብ ጋራ አዝ:-ለዚህ ነው ኩራት ስላለኝ አባት ለዚህ ነው ትምክቴ ስላለኝ አባት አባት ስላለኝ አባት (2x) ቆይቷል ከገባኝ እውነቱ ወንጌል እንደሆነ መድሃኒቱ ሌላ ሌላ ማየት ትቻለሁ ኢየሱስ ያድናል ብያለሁ (2x) ሌላ ሌላ ትቻለሁ ጌታ ጌታን ብያለሁ (2x) ቀለለብንና የዓለም ነገር የሰማይ የሰማይ ያስብለኝ ጀመር መዝገቤ ተቀምጦ በበጉ ከተማ ልቤም በዚያ ቀረ ምንም ሳያቅማማ አዝ:-ለዚህ ነው ኩራት ስላለኝ አባት ለዚህ ነው ትምክቴ ስላለኝ አባት አባት ስላለኝ አባት (2x) በጠማማው ዓለም ኢየሱስን ይዤ (አሃሃሃ) ኢየሱስን የዤ አገለግላለሁ መቅደሱ ገብቼ (አሃሃሃ) መቅደሱ ገብቼ በሚያልፈው ዓለም ኢየሱስን ይዤ (አሃሃሃ) ኢየሱስን የዤ አገለግላለሁ መቅደሱ ገብቼ (አሃሃሃ) መቅደሱ ገብቼ አዝ:-ለዚህ ነው ኩራት ስላለኝ አባት ለዚህ ነው ትምክቴ ስላለኝ አባት አባት ስላለኝ አባት (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection