Song Lyrics

ዝናዬ

ልቤ ሰላም ሲያጣ መከራው ሲበዛ ወደማን አያለሁ ኢየሱስ ካንተ ሌላ ልቤ ሰላም ሲያጣ ወጀቡ ሲበዛ ወደማን አያለሁ የሱስ ካንተ ሌላ ወየሁ ጠፋሁ ብዬ ሳለቅስ ሳነባ ብቻዬን ነኝ ብዬ ስቆዝም ስከፋ የዘላለም አምላክ ኢየሱስ ደረሰልኝ የልቤን ተናግሮ በሰላም ሂድ አለኝ አወድሃለሁ አወድሃለሁ አወድሃለሁ ሚገባኝ ይሄ ነው (2x) ዝና ዝናዬ ዝና ዝናዬ አንተው ነህና (2x) ባገልግሎቴ ላይ ዝናዬ ክብር ያሳየኅኝ ዝናዬ የማዕረግ ልብሴ ዝናዬ የክብር ሽልማት ዝናዬ ብኖር ላትጠቀም ሞቼ ላትጎዳ በደምህ ከፈልከው የሕይወቴን ዕዳ በደለኛው ልቤን በደምህ ቀድሰህ ሕይወትን ሸለምከኝ ደህንነት አልብሰህ ጉድጓዴን ስቆፍር ድንበሬን ልገፋ ምሕረትህ ገደበኝ ታዝቦ ስገፋ ነፍሴም ተመለሰች ከርስቷ ግዛት በመስቀሉ ስራህ በጻድቁ ሞት አወድሃለሁ አወድሃለሁ አወድሃለሁ ሚገባኝ ይሄ ነው (2x) ዝና ዝናዬ ዝና ዝናዬ አንተው ነህና (2x) ባገልግሎቴ ላይ ዝናዬ ክብር ያሳየኅኝ ዝናዬ የማዕረግ ልብሴ ዝናዬ የክብር ሽልማት ዝናዬ የሰጠኝን ላጣ የእጁን ተመኝቼ ምሕረትን ስጠማ ፍሬዋን በልቼ የጽድቅን ጥያቄ በልጁ መልሶ ፈቃዱን አጸና መርገሜን ፈውሶ ዝና ዝናዬ ዝና ዝናዬ አንተው ነህና (2x) ባገልግሎቴ ላይ ዝናዬ ክብር ያሳየኅኝ ዝናዬ የማዕረግ ልብሴ ዝናዬ የክብር ሽልማት ዝናዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection