እንዳልሸበር እንዳልፈራ ከፊቴ ወጥቶ ከእኔ ጋራ አባቴ ጀግና ደግሞ አሸናፊ እኔም ልጁ ነኝ ድልን አድራጊ እኔም ልጁ ነኝ አሃ አሃ ድልን አድራጊ (4x) አዝ፦ጌታዬ ገናና ነው ገናና ነው መንግስቱ ወደር የለው ከሁሉ እርሱ የበላይ ነው እርሱ የበላይ ነው (4x) ኃይላት ሥልጣናት ሁሉንም ገፎ ድል አስለመደኝ ለእኔ ተዋግቶ ፅኑ ቃልኪዳን ከእኔ ጋር ገብቷል ጠላቴ ዛሬ መርዶውን ሰምቷል ጠላቴ ዛሬ አሃ አሃ መርዶውን ሰምቷል (4x) አዝ፦ጌታዬ ገናና ነው ገናና ነው መንግስቱ ወደር የለው ከሁሉ እርሱ የበላይ ነው እርሱ የበላይ ነው (4x) ከፍታ ነው እንጂ አይደለም ዝቅታ ለእኔ ያየው ጌታ (2x) ድርሻዬ ነው ለኔስ ሁልጊዜ ከፍታ ለእኔ ያየው ጌታ (2x) እንዳልሸበር እንዳልፈራ ከፊቴ ወጥቶ ከእኔ ጋራ አባቴ ጀግና ደግሞ አሸናፊ እኔም ልጁ ነኝ ድልን አድራጊ እኔም ልጁ ነኝ ድልን አድራጊ (4x) አዝ፦ጌታዬ ገናና ነው ገናና ነው መንግስቱ ወደር የለው ከሁሉ እርሱ የበላይ ነው እርሱ የበላይ ነው (4x)