የጌታ የጌታ ልጅ የኢየሱስ ልጅ ቀና በል እንጂ የአባቴ የአምላኬ ልጅ የኢየሱስ ልጅ ኮራ በል እንጂ ጠላት ሲቆዝም ያቀርቅር እንጂ ቀና ቀና በል የጌታ ልጅ እርሱን ለፈራው ላከበረው እስከ ሺህ ትውልድ በረከት ነው ጌታን ተማምኖ የለም ዝምታ በእርግጥ ተሰብሯል ይመለክ ጌታ ከዚህ በፊት የለመድኩት የጠየኩት ያሳየሁት ነገር (2x) ዞሮ ገባ እጄ ገባ አልቀረብኝ እግዚአብሔር ሲናገር ነገር ዙፋኑ ስር መቅደሱ ስር ማደሪያው ስር ስለምነው ውዬ (2x) አላፈርኩም አልከሰርኩም ተሳካልኝ ጌታ ጌታን ብዬ (2x) ብዬማ ጌታ አለ ብዬ ብዬማ ታለምአልኜ ብዬማ ነገር ተሳካ ብዬማ እርሱን ለምኜ የኢየሱስ ውለታው የበዛባችሁ ቅኔን ተቀኙለት እልል ብላችሁ ለክብሩ የሚሆን አምጡ ምሥጋና እስቲ ጨምሩለት ቅዱስ ነውና ደግሞ ለጌታ የምን ዝምታ ደግሞ ለጌታ ከበሮ ይመታ ደግሞ ለጌታ ሳመልከው ውዬ ደግሞ ለጌታ ሳመልከው ይነጋ የጌታ የጌታ ልጅ የኢየሱስ ልጅ ቀና በል እንጂ የአባቴ የአምላኬ ልጅ የኢየሱስ ልጅ ኮራ በል እንጂ መንግሥተ ሠማይ የጀግና አገር የእኛም አገር ነች በዚያ እንድንኖር በምድር መቶ እጥፍ በላይ ደስታ ትልቅ ዕድል ነው መሆን የጌታ አክሊል ያገኛል ድል ያነሳው ለእግዚአብሔር ኖሮ የጨረሰው ኢየሱሴን ተቀብሎ . (1) . ጌታ ንጉሥ ያደረገውን ሰውን እንደ እርሱ የለም የታደለ ምስጉን ትውልድ ከሞት ያዳነው ሰው ውኃው ተባርኮለት ደዌ ችግር ተወግዶለት ሞትን ተዘልሎ ተቀምጧል እንደ አንበሳ አርፏል በድፍረት ሕይወት እርሱማ ያመስግነው እርሱማ ባለ ዕዳ ነው እርሱማ ማቁ ተቀዶ እርሱማ ሊዘምረው የኢየሱስ ውለታው የበዛባችሁ ቅኔን ተቀኙለት እልል ብላችሁ ለክብሩ የሚሆን አምጡ ምሥጋና እስቲ ጨምሩለት ቅዱስ ነውና ደግሞ ለጌታ የምን ዝምታ ደግሞ ለጌታ ከበሮ ይመታ ደግሞ ለጌታ ሳመልከው ውዬ ደግሞ ለጌታ ሳመልከው ይነጋ እርሱማ ያመስግነው እርሱማ ባለ ዕዳ ነው እርሱማ ማቁ ተቀዶ እርሱማ ሊዘምረው