አዝ፦ ተይ ነፍሴ የአምላክሽን ቃል ስሚና ግራ ቀኙን ተይውና ኋላ ደግሞ እንዳይቆጭሽ ከአምላክሽ ጋር ተጣልተሽ እርሱ ነው ሚረባሽን ሚያውቅልሽ ከእርሱ ሌላ አትፈልጊ የሚረባሽን አሃሃ አምላክሽ አለ አሃሃ ሚያስብልሽ አሃሃ ግራና ቀኙን አሃሃ ምን አሳየሽ አሃሃ እርሱስ ስለአንቺ አሃሃ ቆስሏልና አሃሃ ሌላ አትፈልጊ አሃሃ አይጠቅምምና ኤሄ ሞልቶ ላይሞላ ኤሄ ለዓለም ነገር ነፍሴ አትጨነቂ የቀረው ይቅር ኤሄ ሁሉ ከንቱ ነው ኤሄ የከንቱ ከንቱ ነፍሴ ቃሉ ይሻላል የእርሱ የአንደበቱ እኔ ደግሞ ወይ ለራሴ ቀን አስቦ??? ለክብር ነፍሴ የሰጠኀኝ ፈራሽ ሥጋዬ ላይሆነኝ መከበሪያዬ አባትዬ ባክህ አደራ በዘመኔ ስራህን ልስራ አስከብሬህ ልኑር ለክብርህ ስምህ በእኔ ላይ እንዲጠራ አዝ፦ ተይ ነፍሴ የአምላክሽን ቃል ስሚና ግራ ቀኙን ተይውና ኋላ ደግሞ እንዳይቆጭሽ ከአምላክሽ ጋር ተጣልተሽ እርሱ ነው ሚረባሽን ሚያውቅልሽ ከእርሱ ሌላ አትፈልጊ የሚረባሽን አሃሃ አታስጨንቂኝ አሃሃ አታውኪኝ አሃሃ ወዲህና ወዲያ አሃሃ አትበይቢኝ አሃሃ የዓለም ብልጭልጭ አሃሃ መልኩ ውበቱ አሃሃ ሁሉም ጠፊ ነው አሃሃ ደርሷል ሰዓቱ ኤሄ ኀጢአት ብትሰሪ ኤሄ ትሞቻለሽ ነፍሴ ጽድቅን ብትሰሪ በሕይወት ትኖሪያለሽ ኤሄ እንዳያዝንብሽ ኤሄ የሞተልሽን ነፍሴ ለጽድቅ ንቂ በሕይወት ለሚያኖርሽን ሥጋ ነቅቶ መንፈስ ቢደክም መንፈስ ነቅቶ ሥጋ ሲደክም ለበረታው ላሸነፈው ብትወግኚ ለበለጠው ነፍሴ ዕውቀት ፍቃድ አለሽ ተገዢለት ለታደገሽ ለግዚአብሄር ለስሙ ኑሪ በሰማይ ቤት ፊቱ እንዳታፍሪ