እረጅሙን ጐዳና በጽድቅ እንዳልሄድኩኝ አንተን እንዳላሳዝን ፊትህ እንደማልኩኝ ዛሬ ምነው ጠፋኝ አቅም አጣን እኔ ነኝ ጥፋተኛ እኔን እኔን ማረኝ ዕንቁዬን ሜዳ ጥዬው ብቻዬን ቀረሁኝ ጌታ ሆይ መልሰኝ ምህረት አድርግልኝ አዝ፦ መልሰኝ ወደድሮዬ መልሰኝ ወዳስተማርከኝ መልሰኝ ወደጓዳዬ መልሰኝ ወደነገርከኝ አንተን ተጣልቼ እንዴት እሆናለሁ ከአንተ ተስማምቼ እኔስ እኖራለሁ ስታበይ ገፅፀኝ ሳጠፋ ቅጣኝ መንፈስህን ከእኔ አትውሰድብኝ አንተ ዝም ካልከኝ ምንስ ይውጠኛል የአንተ ዝምታ እኮ አፍ አለው ያወራል ብቻ ይሁን እንጂ የነገርከኝ ኢየሱስ ያልከኝ እኔስ ከሃሳብህ ጋር እስማማለሁ ይሁን እንዳልከኝ (2x) ብዙ የለፋሁበት ያከማቸሁት ሃብቴ ከእጄ ላይ ተበተነ ሳላውቀው ከጥማቴ የተቀደስኩለት ከዳኝ ማንነቴ አወይ አለመታዘዝ አሻፈረኝ ማለቴ አይረባህም ስትለኝ አንተን አለመስማቴ ዛሬ ግን ገብቶኛል ጎድቶኛል አባቴ አዝ፦ መልሰኝ ወደድሮዬ መልሰኝ ወዳስተማርከኝ መልሰኝ ወደጓዳዬ መልሰኝ ወደነገርከኝ አንተን ተጣልቼ እንዴት እሆናለሁ ከአንተ ተስማምቼ እኔስ እኖራለሁ ጴጥሮስሓዋርያው አልክድም ያለው ዶሮ ሳይጮህ በፊት ሶስት ጊዜ ነው የካደው ነገር ግን ምህረትህ እጅግ ስለበዛ አስበህ ለወጥከው ሰው አደረከው ጌታ ብቻ ይሁን እንጂ የነገርከኝ ኢየሱስ ያልከኝ እኔስ ከሃሳብህ ጋር እስማማለሁ ይሁን እንዳልከኝ (2x)