ስለማልችል ያለ አንተ መኖር አትሂድብኝ ባክህ ጌታ ሆይ እኔስ ያለ አንተ አልችልምና ችላ አትበለኝ ክብሬን ክብሬ ነህና አዝ፦ አልችልበትም እኔስ አይሆንልኝም እኔስ ያላንተ መኖር (2x) ዓይኔን በእጄ አልወጋም የጠራኝን ትቼ እንዴት ነው ምኖረው ከአንተ ተለይቼ ሌላው ሚመካበት አለው ብዙ ነገር ለእኔ ግን አንተ ነህ የመኖሬ ትርጉም አዝ፦ አልችልበትም እኔስ አይሆንልኝም እኔስ ያለአንተ መኖር ሲከብደኝ ብቸኝነቴ ሳዝን ስተክዝ በቤቲት ቅዱሱን መንፈስ አልኩኝ እባክህ አትሂድብኝ የሰው ጥማቱ ሌላ ነው የኤኔ ግን አንድ ብቻ ነው ያላንተ መኖር አልችልም ለአፍታ እንኳን አትተወኝ ስለማልችል ያለ አንተ መኖር አትሂድብኝ ባክህ ጌታ ሆይ እኔስ ያለ አንተ አልችልምና ችላ አትበለኝ ክብሬን ክብሬ ነህና ሳኦል ምን ነክቶት ከሰረ ለሥጋው ምቾት ስለአደረ አጥፋልኝ ብለህ ስትልከው ያማረውን ለኤራሱ አስቀረው በሚያልፈው ነገር ተታሎ በድፍረት ሲጓዝ አይ ብሎ ድምጽህን ንቆ ሲወጣ መንፈስህ ሸሽቶ ተቀጣ አጥፋልኝ ያልከውን አጠፋዋለሁኝ ሰዋልኝ ያልከውን እሰዋዋለሁኝ ዝክሩን ከምድር ላይ መንግሥቱን አፍርሼ አስደስትሃለሁኝ ቃልህን ጠብቄ አዝ፦ አልችልበትም እኔስ አይሆንልኝም እኔስ ያላንተ መኖር (2x)