Song Lyrics

ትርፌማ ቅባት ነው

Ephrem Alemu
Acha Yelelwu
ሥምህ በአፌ ላይ ይጣፍጠኛል ሁሌ ስጠራው ደስ ደስ ይለኛል የትኛው ሥም ነው የተወደደው ጠዋት ተወርቶ ማታ የሚወርደው እንዳየነው የእኔ ኢየሱስ ግን ሥሙ ይለያል ሁሌ ስጠራው ደስ ደስ ይለኛል ጠረነ ልዩ ማዕዛ ያለው የአባትዬ ሥም ልክ እንደ ማር ነው እንደ ማር እንደ ማር ኧረ እንደ ማር (4x) እኔስ ቆርጫለሁ ለጌታ ዘንድሮ ሕይወት ተገለጠ በራ ንብረት ሆኖ ዋጋዬን ተምኜ ስለወጣሁኝ እመቅደሱ ደጃፍ ወስዳችሁ ጣሉኝ ትርፌማ ቅባት ነው ቅባት በመንገዴ ያገኘኛል አልኩኝ ያየኛል አባቴ ዋጋዬን ተምኜው ስለወጣሁኝ እመቅደሱ ደጃፍ ወስዳችሁ ጣሉኝ (3x) አሄ ኦሆ አርዶ የወጣ ሰው ከቶ አይመለስም ጌልጌላ ተነስቶ ቤቴል ላይ አይቆምም ወያሪኮ ወድቆ ዮርዳኖስ ይዘልቃል እጥፍ መንፈስ ይዞ በክብር ይመለሳል ወይ ሊያስችለኝ ውኃ የሚያፈሰው አስራ ሁለቱን በግ በሬ አረደው በሕያው ልብሱ ምን አለ የተከተለው ሞኝ ሆኖ አይደለም ክብር አይቶ ነው ቅባት አይቶ ነው ክብር አይቶ ነው ጌልጌላ ሸለፈትክ የተገረዘው ቤቴል የእግዚአብሔር ቤት የተጸለየው እያሪኮም ይናድ በጩኸት ይፍረስ ዮርዳኖስ ልጠመቅ በመንፈስ ቅዱስ አባናና ፋርፋን አልል እንደ ሰው ዮርዳኖስ ይበልጣል የደፈረሰው ብቅ ትልቅ ብዬል ከለምጽ እነጻለሁ አንተ ያልከኝ ቦታ ፈውስ አገኛለሁ (2x) መዳን አገኛለሁ ዘመኔ እንደ ሻማ እንደ ጧፍ ቢነድ ያንስበታል እንጂ መች ይበዛበት እርሱማ ተዋርዶ በሞቱ አክብሮኝ ለኢየሱሴ ኖሬ እስቲ ይለይልኝ አሸፈተው ልቤን ኢየሱስን ወዶ የሠማይ አስባለኝ የምድሩን አስንቆ ልቤ ትዝታዬም እርሱ ጋር ቀረና ሁሉንም አሳቀኝ የእርሱ በለጠና ክብር በለጠና ቅባት በለጠና ሞኝ ነህ ይሉኛል የታል ሞኝነቴ አተረፈኩኝ እንጂ ምንድን ነው ጉዳቴ ኢየሱስን ይዤ እኔስ አትርፊያለሁ ምድር ተቀምጬ ቤቴ በሠማይ ነው ይኸው ሁለ ልቤን እንካ ውሰደው አንተ ጋር ይቀመጥ የእኔ ከንቱ ነው ሁሉንም ሰብስቤ ለአንተ ሰጠሁና አንተን አንተን አልኩኝ የአንተ በለጠና መንፈስ በለጠና ቅባት በለጠና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection