Song Lyrics

አስታዋሼ

Ephrem Alemu
Acha Yelelwu
ሰው የረሳኝን አስታወስከኝ ከአመድ ከትቢያ ያነሳኀኝ እኔም ስላየሁ ክንድህን ጌታ ደራሽ ነህ ልበልህ (2x) (ደራሽ ነህ) ምድረ በዳውን (ደራሽ ነህ) ያሳለፍከኝ (ደራሽ ነህ) ምንጭን አፍልቀህ አጠጣኀኝ (ደራሽ ነህ) አንዴ ጠጥቼ (ደራሽ ነህ) እንዳልጠማ (ደራሽ ነህ) ሕይወት ሆንክልኝ በሞት ከተማ (ደራሽ ነህ) ጌታ (ደራሽ ነህ) ለእኔ (ደራሽ ነህ) ውዴ ደራሽ ነህ ለእኔ ቃል ሲወጣ ከሰማይ ማን ይቆማል ደጃፉ ላይ (ማን ይቆማል ሄ ማን ይቆማል ደጃፉ ላይ) በአንዲት ጀምበር ደረስክና አፌን ሞላህ በምሥጋና (ማን ይቆማል ሄ ማን ይቆማል) እንዳለፈው ታለፈ አበሳዬ ተረሳ (ማን ይቆማል ሄ ማን ይቆማል ደጃፉ ላይ) እኔም ዛሬ ወግ ደረሰኝ የአስታዋሼን ስሙን ላንሳ (ማን ይቆማል ሄ ማን ይቆማል) አዝ፦ አስታዋሼ የእኔ ኧረኛ ሰው ሲረሳኝ አሰብከኛ አስታዋሼ የእኔ ዳኛ ሰው ሲረሳኝ አሰብከኛ (2x) ሰው የረሳኝን አስታወስከኝ ከአመድ ከትቢያ ያነሳኀኝ እኔም ስላየሁ ክንድህን ጌታ ደራሽ ነህ ልበልህ (2x) (ደራሽ ነህ) ምድረ በዳውን (ደራሽ ነህ) ያሳለፍከኝ (ደራሽ ነህ) ምንጭን አፍልቀህ አጠጣኀኝ (ደራሽ ነህ) አንዴ ጠጥቼ (ደራሽ ነህ) እንዳልጠማ (ደራሽ ነህ) ሕይወት ሆንክልኝ በሞት ከተማ (ደራሽ ነህ) ጌታ (ደራሽ ነህ) ለእኔ (ደራሽ ነህ) ውዴ ደራሽ ነህ ለእኔ ኢየሱሴ ባታያኝ ማን ነበረ የሚያየኝ (ማን ነበረ ቆይ ማን ነበረ የሚያየኝ) ግራ ገብቶኝ ስንገላታ ደረስክልኝ የእኔ ጌታ (ማን ነበረ ሄ ማን ነበረ) እነዛ እጆችህ ይባረኩ እኔን አቅፈው ያሳደጉ (ማን ነበረ ቆይ ማን ነበረ የሚያየኝ) አደረግከኝ ጭቅርቅር ተላይ ይፈር ያቀርቅር (ማን ነበረ ሄ ማን ነበረ) አዝ፦ አስታዋሼ የእኔ ኧረኛ ሰው ሲረሳኝ አሰብከኛ አስታዋሼ የእኔ ዳኛ ሰው ሲረሳኝ አሰብከኛ (2x) እንዴት አስታወስከው ያንን ሰው (2x) እንዴት አስታወስከው ያንን ሰው (2x) እንዴት አስታወስከው ያንን ሰው (2x) እንዴት አስታወስከው ያንን ሰው (2x) አዝ፦ አስታዋሼ የእኔ ኧረኛ ሰው ሲረሳኝ አሰብከኛ አስታዋሼ የእኔ ዳኛ ሰው ሲረሳኝ አሰብከኛ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection