እረኛዬ x2 ነህ እኛዬ ነህ የነፍሴ ጠባቂን ከአንበሳና ከድብ ከአውሬው ከነጣቂ ያ ዳዊት እውነቱን እኮ ነው ኧረኛዬ ብሎ የዘመረው ከአንበሳ ከድብ ስታተርፈው ያለአንተ ማን አስተዋሽ አለው ገበታን አዘጋጀህለት ንግስናን አንተው ስታነግሰው ባይዘምር ይገርመኝ ነበር የእኔም ታሪክ እንደዳዊት አለ አባትዬ አባብዬ ነህ አባትዬ ነህ የነፍሴ ጠባቂን ከአንበሳና ከድብ ከአውሬው ከነጣቂ መሰማሪያን ከአገኘሁ ቆየው እረኛዬን ስለተጠጋሁ በክንፎቹ ጥላ ስር ሆኜ እኖራለሁ ተደላድዬ (ለምን ቢባል) እረኛዬን ይዤ (ለምን ቢባል) ቅጥሩን እዘላለሁ (ለምን ቢባል) ሓሩሩ እንዳይጐዳኝ (ለምን ቢባል) ጥላን አግኝቻለሁ (2x) አዝ፦ እረኛዬ (2x) ነህ እረኛዬ ነህ የነፍሴ ጠባቂን ከአንበሳና ከድብ ከአውሬው ከነጣቂ ከሰማይ ወደቀብኝ እጣ እንዳጥን ልዘምር ለጌታ ጥሪ ነው የእርሱ ያደረገኝ ለሌላው መሆን አቃተኝ ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ የለየኝ ዘማሪ ነህ ብሎ ዕድሜዬን ለእርሱ ሰጥቻለሁ ሳመልከው ስዘምር እኖራለሁ አባትዬ አባብዬ ነህ አባትዬ ነህ የነፍሴ ጠባቂን ከአንበሳና ከድብ ከአውሬው ከነጣቂ ቸርነቱና ምህረቱ ሁልጊዜ ይከተሉኛል በእግዚአብሔር ቤት ለዘላለም እኖራለሁ ምን ያስፈራኛል (እኔ አልፈራም) በትሩ ምርኩዞ (እኔ አልፈራም) እነርሱ ያጽናኑኛል (እኔ አልፈራም) ከፊቴ ገበታ (እኔ አልፈራም) ተዘጋጅቶልኛል (እኔ አልፈራም) ጽዋዬማ እርሱ ዘንድ (እኔ አልፈራም) የተረፈ ነው (እኔ አልፈራም) ኢየሱስን ይዤ (እኔ አልፈራም) ምን እሆናለሁ