Song Lyrics

ዘምር አለኝ

Ephrem Alemu
Acha Yelelwu
ጠላት የጻፈው የሞት ደብዳቤ ተቀዶ ሳየው ደስ አለው ልቤ (ደስ አለው ልቤ) ጠላቴን ጥሎ ስላሳየኝ ልቤም በደስታ ዘምር አለኝ (ዘምር አለኝ) አዝ፦ ዘምር (2x) (ዘምር አለኝ) አምልክ (2x) (አምልክ አለኝ) ስገድ (2x) (ስገድ አለኝ) ለእርሱ ዘምር (ዘምር አለኝ) ሸንጐ ሰብስቦብኝ መክሮብኛል ዝቶብኛል ሰበብ ፈልጐብኝ ይዋጋኛል ይዞረኛል የሚጠብቀኝ ስለማይተኛ እኔም አርፌ እስቲ ልተኛ ዙሪያዬ ቢዞር ቢሽከረከረ እኔ እንደሆነ አለኝ ክብር የተቀባ ሰው ሰልፉ ብዙ ነው ነገር ግን ጌታ ከእኔ ጋራ ነው አዝ፦ ዘምር (2x) (ዘምር አለኝ) አምልክ (2x) (አምልክ አለኝ) ስገድ (2x) (ስገድ አለኝ) ለእርሱ ዘምር (ዘምር አለኝ) የሲኦል በር ሲዘጋ ለእኔ ሌቱ ሲነጋ (ሲነጋ) ሲነጋ (ሲነጋ) ጠላቴ ሲመሽበት ለማጁ ሰው በራለት ነጋለት (ነጋለት) በራለት (በራለት) ደሙ ነው ምልክቴ አይገባል ሞት እቤቴ ከቤቴ (ከቤቴ) እቤቴ (ከቤቴ) ያሳረገኝ ደሙ ነው ስለዚህ እዘምራለሁኝ ለጌታ (ለጌታ) በደስታ (በደስታ) ምልክት አለብኝ የኢየሱስ ደም በግምባሬ ይፈራኛል ጠላት ከቶ አይቀርብም በሰፈሬ በአጠገቤ ሺ በቀኝ አስር ሺ እየጫረልኝ??? ሆንኩኝ ድል ነሺ ዙሪያዬ ስሜ በደሙ ታጥሯል ቅዱስ መንፈሱ ይጠብቀኛል በድል ወጥቼ በድል እገባለሁ የእኔ ከለላ የእሳት ቅጥር ነው ጠላት የጻፈው የሞት ደብዳቤ ተቀዶ ሳየው ደስ አለው ልቤ (ደስ አለው ልቤ) ጠላቴን ጥሎ ስላሳየኝ ልቤም በደስታ ዘምር አለኝ (ዘምር አለኝ) አዝ፦ ዘምር (2x) (ዘምር አለኝ) አምልክ (2x) (አምልክ አለኝ) ስገድ (2x) (ስገድ አለኝ) ለእርሱ ዘምር (ዘምር አለኝ) ምህረቱ በዝቶብኝ በሕይወቴ አለሁኝ የእኔ ነው የምለው ምንም ነገር የሌለኝ በቃ ማርኮኛል ተማርኬያለሁ ለፍቅሩ ብዛት እጄን ሰጥቻለሁ ከአሁን በኋላ የምኖረው ለጌታ ኢየሱስ ልስሙ ነው ዕድሜ ቀጥሎ ኑር ስላለኝ እኔም ለስሙ እኖራለሁኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection