Song Lyrics

ከአንተ ጋር

Ephrem Alemu
Acha Yelelwu
አዝ፦ ከአንተ ጋር ልኑር አንተ ጋር ከአንተ ጋር ኢየሱስ ልኑር አንተ ጋር ከአንተ ጋር ያለ አንተ አይሆንልኝም ከአንተ ጋር ብቻዬን አያምርብኝ ከአንተ ጋር ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር ባልበላ እጠግባለሁ ከአንተ ጋር (2x) በንጉሥ ጮማ ከኖሩ ቆሎ ቆርጥመው ያደሩ አስር እጅ አማረባቸው ከአንተ ጋራ የወገኑ በምድር ተጨምጭቦልኝ በሰማይ ከምታፍርብኝ ይቅርብኝ ሁሉም ይቅር ከአንተ ጋራ ብቻ ልኑር መራብን አውቃለሁ መጥገብን ማግኘትን አውቃለሁ ማጣትን እኔ ማይሆንልኝ ማያምርብኝ ያላንተ መኖር ነው የታውቅክልኝ ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር ባልበላ እጠግባለሁ ከአንተ ጋር (2x) አዝ፦ ከአንተ ጋር ልኑር አንተ ጋር ከአንተ ጋር ኢየሱስ ልኑር አንተ ጋር ከአንተ ጋር ያለ አንተ አይሆንልኝም ከአንተ ጋር ብቻዬን አያምርብኝ ከአንተ ጋር ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር ባልበላ እጠግባለሁ ከአንተ ጋር ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር ባልጠጣ ያረካኛል ከአንተ ጋር ቢቃጠል ወጣትነቴ ቢነድም ለአንተ ጉልበቴ ቢቀናም ክፉ ጠላቴ ለአንተ ብቻ ነው አባቴ የሰው ልጅ ዕድሜ ሰንቃላ ሰማንያ አመት የማይሞላ ድካም ነው ከዚያ በኋላ አልሆንም እኔስ ተላላ ሺህ ዓመት አልኖርም በምድር እንደእንፋሎት ነው የሰው ልጅ ዘመን በቃ ለአንተ ክብር ልኑርና ዘመኔን ጨርሰው ጌታ ቀድስና ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር ባልበላ እጠግባለሁ ከአንተ ጋር (2x) ሙሴ አይቶ ብድራቱን የልጅ ልጅ ንግስናውን ንቆታል ለእግዚአብሔር ብሎ አልጋውን ክብሩን ተምኖ ኧረ ለእኔ ትልቅ እድል ነው ከአንተ ጋር ብዬ ምኖረው እንኳን አገልጋይ ሆኜ ይበቃል ባሪያ መባሌ የእኔ መጨረሻ ጥግ እርካታዬ መገኘትህ ሲኖር በቤት በጓዳዬ ያን ጊዜ በፍፁም ልቤ ኧረካለሁ ፊትህን እያየሁ ሁልጊዜ እጠግባለሁ ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር ባልበላ እጠግባለሁ ከአንተ ጋር ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር ባልጠጣ ያረካኛል ከአንተ ጋር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection