አዝ፦ ክንዱ ነው ታሪኬን የለዋወጠው ጣቱ ነው ነገሬን የቀያየረው (2x) አይቻለሁ በአንተ ሸለቆው ውኃ ሲሞላ ጌታ ስትሆነኝ ከለላ (2x) አንገት እንድደፋ እንዳቀረቅር ከሰው በታችን ሆኜ ነበር ምኞቱ ጠላቴማ ሰው ለማድረግ ከንቱ አወይ ልፋቱ የማመልከው ጌታ እጄን ያዘኝ እንደገና አነሳኝ ዳግም አቆመኝ ማነው ማነው ማነው ኧረ ማነው ማነው ማነው ማነው ማነው እኮ ማነው ማነው እሃሃሃ እግዚአብሔር እኮ ነው ለእኔ የደረሰው (2x) አዝ፦ ክንዱ ነው ታሪኬን የለዋወጠው ጣቱ ነው ነገሬን የቀያየረው (2x) አይቻለሁ በአንተ ሸለቆው ውኃ ሲሞላ ጌታ ስትሆነኝ ከለላ (2x) በዚያ በጭንቅ ቀን በቁርጥ ጊዜ በመከራ ሰዓት ከጐኔ የሚቆም አይዞህ የሚለኝ አጋዥ ባጣሁበት የናዝሬቱ ኢየሱስ ወደ እኔ ሲመጣ ጉልበቴም ከፍ አለልኝ አቅሜም በረታ ማነው ማነው ማነው ኧረ ማነው ማነው ማነው ማነው ማነው እኮ ማነው ማነው እሃሃሃ እግዚአብሔር እኮ ነው ለእኔ የደረሰው (2x)